አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ግብር ከፋዮች ደረሰኝ አሳትመው መጠቀም የሚችሉበት መንገድ

ግብር ከፋዮች ደረሰኝ አሳትመው መጠቀም የሚችሉበት መንገድ
ግብር ከፋዮች ደረሰኝ አሳትመው መጠቀም የሚችሉበት መንገድ

በታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 149/2011 መሰረት በሀገር ውስጥ ከሚፈጸሙ የዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዥዎች ክፍያ ላይ ግብር ቀንሶ የማስቀረት ኃላፊነት ያለበት አካል ስለሚሰጠው ደረሰኝ አይነትና ስለፈቃድ አሠጣጥ የሚከተለውን ይላል፡-

1. ከተከፋይ ሂሳብ ላይ የንግድ ትርፍ ግብር ወይም የኪራይ ገቢ ግብር ቀንሶ እንዲያስቀር ኃላፊነት የተሰጠው የፌደራል መንግስት ባለ በጀት መስሪያ ቤት ቀንሶ ለሚያስቀረው ግብር የሚሰጠው ደረሰኝ የሚታተመው በገንዘብ ሚኒስቴር ይሆናል፡፡



2. ከተከፋይ ሂሳብ ላይ የንግድ ትርፍ ግብር ወይም የኪራይ ገቢ ግብር ቀንሶ እንዲያስቀር ኃላፈነት የተሰጠው የክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ባለበጀት መስሪያ ቤት ቀንሶ ለሚያስቀረው ግብር የሚሰጠው ደረሰኝ የሚታተመው በክልል ወይም በከተማ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ይሆናል፡፡

3. በተራ ቁጥር ሁለት የተገለጸው ቢኖርም በተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት /integrated financial management information system/ የሚጠቀሙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለሚያከናውኑት ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ታትሞ የሚወጣ ደረሰኝ ይሰጣሉ፡፡



4. በሀገር ውስጥ ከሚፈጸሙ የእቃ እና አገልግሎት ግዥዎች ክፍያ ላይ የንግድ ትርፍ ግብር እና የኪራይ ገቢ ግብር ቀንሰው የሚያስቀሩ ሌሎች አካላት ቀንሰው ለሚስቀሩት ግብር የሚሰጡት ደረሰኝ የሚታተመው የሚመለከተው የታክስ ባለስልጣን በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ይሆናል፡፡
ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

(ምንጭ – ገቢዎች ሚኒስቴር – የካቲት 10/2014)

Related Post