አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ድርጅትዎን ከሀሰተኛ ደረሰኝ ለመታደግ የሚጠቅሙ አንዳንድ መረጃዎች

ድርጅትዎን ከሀሰተኛ ደረሰኝ ለመታደግ የሚጠቅሙ አንዳንድ መረጃዎች
ድርጅትዎን ከሀሰተኛ ደረሰኝ ለመታደግ የሚጠቅሙ አንዳንድ መረጃዎች

ድርጅትዎን ከሀሰተኛ ደረሰኝ ብሎም ከሚያስከትለው ተጠያቂነት ለመታደግ የሚጠቅሙ አንዳንድ መረጃዎች።

1. ደረሰኝ ሲቀበሉ ደረሰኝ ላይ ያለው መረጃ ሻጩ ከለጠፈው የንግድ ስምና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ጋር ያመሳክሩ ሲያመሳክሩ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩ ከተቀበሉት ደረሰኝ ጋር መረጃው ከተለያየ ህገ-ወጥ ድርጅት መሆኑ ማወቅ ይችላሉ፤

2. ዕቃ/አገልግሎት የሸጠሎትን ድርጅት አድራሻ ማወቅ አለብዎት የሻጩን አድራሻ ማወቅ ህገ-ወጥ ሆኖ ሲገኝ በህግ ለመጠየቅ ያግዝዎታል፤
3. ለድርጅትዎ ባለሙያዎች ስለታክስ ግዴታዎች ማስገንዘብ አለብዎት ለድርጅትዎ ባለሙያዎች ስለታክስ ግዴታ እንዲያውቁ ካደረጉ በግብይት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለማድረግ ያግዝዎታል፤

4. ክፍያ ሲከፍሉ በጥሬ ገንዘብ ከመፈፀም ይልቅ በባንክ ይጠቀሙ ክፍያ በባንክ በኩል መፈፀም ባህል ማድረግ ከቻሉ የተቀባዩን/የሻጩን ዱካ ለማወቅ ያስችላል፤
5. ስራ አስኪያጆች/የድርጅት ባለቤቶች የድርጅታቸውን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በቅርበት መከታተል አለባቸው ይህም በድርጅትዎ ባለሙያዎች ህገ-ወጥ ድርጊት እንዳይፈጸም ያስችልዎታል፡፡ በመሆኑም ሁል ጊዜ የድርጅትዎን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በቅርበት መከታተል አለብዎት፤

6. የድርጅትዎን አሰራር በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ አሰራርን በማዘመን ለስራዎ መቀላጠፍን ከመጨመሩም በላይ ለህገ-ወጥ ስራ በር የሚከፍቱ አሰራሮችን ለማስቀረት ይረዳል፤

7. በግብይት ወቅት የደላላ ጣልቃ ገብነትን መቀነስ፡፡ ግብይትን ያለሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት መፈፀም ስለሻጩ ማንነት ለማወቅ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ጣልቃ ገብነትን በተቻለ መጠን ማስቀረት ጠቃሚ ይሆናል፤

8. ሻጩ ድርጅት የተሰማራበት የንግድ ዘርፍ እርስዎ የሚገዙትን ዕቃ/አገልግሎት ማቅረብ የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ አለብዎ፡፡ በድርጅቶች የሚቀርቡ ደረሰኞች ተቀባይነት የሚኖራቸው የተሰማሩበት የንግድ ዘርፍ ዕቃው/አገልግሎቱ እንዲሸጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን ነው፡፡ ለምሳሌ ሲሚንቶ ሻጭ ልብስ ሸጫለሁ ብሎ ደረሰኝ ቢቆርጥ ተቀባይነት አያገኝም፤

9. አጠራጣሪ ደረሰኝ ሲያግጥምዎ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የገቢዎች ቅርንጫፍ በመሄድ ስለድርጅቱ ትክለኛነት ያረጋግጡ፡፡ ሀሰተኛ ደረሰኝ የሚያሰራጩ ህገ-ወጦች በመኖራቸው ግብይት በሚፈፅሙበት ወቅት አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥምዎ ክፍያ ከመፈፀምዎ አስቀድመው የገቢዎች ባለሙያዎችን ያማክሩ፡፡

Related Post