አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች – ክፍል አንድ

ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች - ክፍል አንድ
ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች - ክፍል አንድ

ያለገደብ እና በገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አሉ ከእነኚህ ውስጥ ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎችን ክፍል አንድ መረጃ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

1. ተቀጣሪ ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤
2. የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤

3. በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤
4. በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤

5. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው፡- ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ እና ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ

6. በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን የሚሰጥ ሽልማት:-
• አንድን ቴክኖሎጅ ለማሻሻል፣ አዲስ የፈጠራ ስራ በመስራት ወይም ወጪን ለመቀነስ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ስራ ላይ በማዋል የሚሰጥ ሽልማት
• በአለም አቀፍ ደረጃ በሚደረግ ውድድር አገርን ወክሎ ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በህግ በተቋቋመ ድርጅት በሚደረግ ማንኛውም ውድድር የሚሰጥ ሽልማት
• በፌደራል፣ በክልል፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር መንግስት የላቀ የስራ ክንውን ላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚሰጥ ሽልማት ሲሆን ሽልማቱ ከገቢ ግብር ነጻ ሊሆን የሚችለው ከፈጠራ ስራው ጋር ግንኙነት ያለው የመንግስት አካል ለፈጠራ ስራው እውቅና የተሰጠው ወይም የፈጠራ መብት ሲኖረው ነው

7. በተቀጣሪው ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤
8. ስጦታው የመቀጠር፣ የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
9. በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤
10. ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤
ቀጣዮቹን በቀጣይ ክፍል ይጠብቁን፡፡

(ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር)

Related Post