አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የወዳደቁ የዉሀ መያዣ ፕላስቲኮች እንዴት የመስፍንን ህይወት ቀየሩ

የወዳደቁ የዉሀ መያዣ ፕላስቲኮች እንዴት የመስፍንን ህይወት ቀየሩ
የወዳደቁ የዉሀ መያዣ ፕላስቲኮች እንዴት የመስፍንን ህይወት ቀየሩ

አርብ ጠዋት ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ገደማ ነው መስፋንና ጓደኞቹ አዲስ አበባ አደይ አበባ ስታዲየም አከባቢ የወዳደቁ የውሀ መያዣ ፕላስቲካችን በማዳበሪያ እየጠቀጠቁ ነው።ይህ ለነሱ የዘወትር ተግባራቸው ነው።

ወጣት መስፋን ተሾመ የ25 አመት ወጣት ሲሆን ተወልዶ ያደገው ሲዳማ ወንዶ ከተማ ነው ትምርቱን እስከ 10 አጠናቆ በተወለደበት ከተማለይ የሞተር ስራ ቢጀምርም ለኪሳራ በመዳረጉ በ2011 ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በ አየር መንገድ አከባቢ በ 150ብር ተቀጥሮ የቀን ስራ በመስራት አጠራቅሞ አሁን ወዳለበት ስራ ለመግባት ችሉዋል። የወዳደቁ ኘላስቲክ፣ብረትና ጠርሙሶችን በመሰብሰብ ለድርጅት ማስረከብ ጀመረ ይህን ስራ ከጀመረ አንድ አመት ከምስት ወር ገደማ ይሆነዋል።

የወዳደቁ የዉሀ መያዣ ፕላስቲኮች እንዴት የመስፍንን ህይወት ቀየሩ
የወዳደቁ የዉሀ መያዣ ፕላስቲኮች እንዴት የመስፍንን ህይወት ቀየሩ

መስፋንና ጓደኞቹ የሚሰሩበት አከባቢ ሰዎች ተፀይፈው አፋንጫቸውን ሸፋነው የሚያልፉበት፣ከተማዋን በማፅዳት ሂደት ውስጥ የሚለቀመው የውሀ መያዣ ፕላስቲክ ስቡስቡ የተከማቸበት ቢሆንም እነሱግን ከመስሪያ ቦታ አልፈው መደሪያ ሆኗቸዋል።ይህ ስፋራ ለመዲናዋ ፅዳት ወገብ መሆኑን ዘንግተውት ያከባቢው ህብረተሰቦች አከባቢውን እንዳቆሸሹ ቢቆጥሩዋቸውም፣ከመንግስት አካላት የተነሱ ትእዛዝ እያስተናገዱም ቢሆን ተግተው በማፅዳት የመዲናችንን ውበት እየጠበቁ ይገኛሉ።
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=_8jTy7sTgIA[/embedyt]
እነዚህ ወጣቶች የስራጣን ሰበብን ወዲያ በመጣል ሰው የተፀየፈውን ቆሻሻ አፅድተው ለለት ጉርስ እንዳያጡ፣ማጅራት እንጃይመቱ፣እንዳይለምኑ የልቁንም ከስራ ፈጣሪነት አልፈው የመዲናዋ ፅዳት ተገን ሆነው ዘወትር ይተጋሉ።

Related Post