አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የኤክሳይዝ ታክስ እና መዝገብ

የኤክሳይዝ ታክስ እና መዝገብ
የኤክሳይዝ ታክስ እና መዝገብ

የኤክሳይዝ ታክስ የመክፈል ግዴታ የተጣለበት ማናቸውም ሰው የሂሳብ መዝገብ የመያዝ እና ጠብቆ የማቆየት ግዴታ አለበት፡፡

በዚህ መሠረት መያዝ ያለበት የሂሳብ መዝገብ:-
1. በሚነበብ እና ሊጠፋ በማይችል አኳኋን በጽሕፈት መሣሪያ የተዘጋጀ፣ የታተመ ወይም የተፃፈ ሊሆን የሚገባው ሲሆን፣ ከመጽደቁ በፊት የተደረገ እርማት ወይም ለውጥ ሲኖር የተደረገውን ለውጥ ወይም እርማት በትክክል ለማወቅ የሚያስችል፤ እርማቱን ያከናወነው ሰው ፊርማ እና የታረመበት ቀን የተፃፈበት፣

2. በተፈቀደ አኳኋን በኤሌክትሮኒክ ወይም በሌላ መንገድ የተዘጋጀ እና በተፈቀደው አኳኋን ካልሆነ በስተቀር ለውጥ ያልተደረገበት መሆን አለበት፡፡

ሚኒስቴሩ በአዋጁ ወይም በመመሪያ ከተመለከተው ውጪ የተዘጋጀን የሂሳብ ሰነድ ወይም ማስረጃ ላለመቀበል ወይም በዚህ ሰነድ መሠረት ሥራዎችን ላለማከናወን ይችላል፡፡ በተጨማሪም ማናቸውም የሂሳብ ሪፖርት ሊቀርብ የሚገባበትን ቅጽ ወይም ለአፈፃፀም ተቀባይነት የሚኖራቸውን ሰነዶች ዓይነት ሊወስን ይችላል፡፡

(ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር)

Related Post