አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

የኤክሣይዝ ታክስ ምንድነው?

የኤክሣይዝ ታክስ ምንድነው
የኤክሣይዝ ታክስ ምንድነው

በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 እና በመመሪያ ቁጥር 67/2013 መሠረት የተወሰኑ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች በሚመረቱበት፣ በሚሸጡበት ወይም ጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ የሚከፈል ታክስ ሲሆን፤ እንደሀገራችን በኢትዮጵያ በተመረቱ ወይም ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ የተመረጡ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ላይ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ አይነት ነው፡፡

የኤክሣይዝ ታክስ የሚጣልባቸው ዕቃዎች ባህሪያት
– የቅንጦት ዕቃዎች – መሠረታዊ ያልሆኑ የኢኮኖሚ ደረጃን ለማሳየት ጥቅም ላይ የሚውሉ፡፡ ምሳሌ፤- ሽቶ፣ ኮስሞቲክ
– ጉዳት የሚያስከትሉ ዕቃዎች – በተጠቃሚው ጤና ማህበራዊ ኑሮ እና ኢኮኖሚ ላይ ችግር የሚያስከትሉ ዕቃዎች፡፡ ምሳሌ፡- ሲጋራ፣ አልኮል መጠጦች፣
– ፍጆታቸው የማይቀንስ ዕቃዎች:- ዋጋቸው በመጨመሩ ምክንያት እምብዛም የፍላጐት/የፍጆታ መቀነስ የማይታይባቸው ዕቃዎች፣ ምሳሌ፤- ጨው፣ስኳር
የኤክሳይዝ ታክስን ስለማሳወቅ
– በማናቸውም አንድ ወር የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈል ቢሆንም ባይሆንም የእያንዳንዱን ወር ሂሳብ አምራቹ በሚቀጥለው ወር እስከ 30ኛው ቀን ማስታወቅ አለበት፡፡
– ማስታወቂያው የእያንዳንዱን ምርት አይነት፤ ለሽያጭ ወጥቶ ሳይሸጥ የተመለሰውን በሙሉ ማካተት ይኖርበታል፡፡
ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ የተደረጉ እቃዎች
– ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ዕቃዎች
– በታክስ ባለስልጣኑ ፍቃድ ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ የተደረጉ ዕቃዎች
– ከኤክሣይዝ ታክስ ነፃ የመሆን መብት ላላቸው አካላት የሚሸጡ ዕቃዎች
– ለኢኮኖሚያዊ፣ ለማህበራዊና ለአስተዳደራዊ ምክንያቶች በሚኒስቴሩ ነፃ የተደረጉ ዕቃዎች
– ለህክምና አገልግሎት እንዲውል ለሰው በመጠጥነት አገልግሎት ሊሰጥ በማይችልበት አኳኋን የተመረተ አልኮል
– በሚከተለው ሁኔታ በአደጋ የጠፉ ወይም የተበላሹ ዕቃዎች
– በመጫን እና በማውረድ ጨምሮ እቃዎቹ ከፋብሪካ በመውጣት ላይ ባሉበት ጊዜ
– በአምራች ፋብሪካ ውስጥ ባሉበት ጊዜ እቃዎቹ ኢትዮጵያ
ከመድረሳቸው በፊት በአውሮፕላን/ በመርከብ በመጓጓዝ ላይ ባሉበት ጊዜ፡፡

Related Post