አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የታክስ ስሌት የሚሻሻልባቸው ምክንያቶች

የታክስ ስሌት የሚሻሻልባቸው ምክንያቶች
የታክስ ስሌት የሚሻሻልባቸው ምክንያቶች

ማንኛውም ታክስ ከፋይ እራሱ አስልቶ ያቀረበውን የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ የታክስ ሚኒስቴሩ ሲፈቅድለት ሊያሻሽል እንደሚችል በአዋጅ ተደንግጓል፡፡

የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለማሻሻል በታክስ ከፋዩ ማመልከቻ ሲቀርብ ማሻሻያው ስለሚፈቀድበት ሁኔታ ግልጽ አሰራረር ማስቀመጥ በማስፈለጉ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 29 በተሠጠው ስልጣን መሰረት መመሪያ አውጥቷል፡፡



መመሪያው ታክስ ከፋዩ የሚያቀርበውን የራስ ታክስ ስሌት እንዲሻሻል ስልሚፈቀድበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ ሲሆን መመሪያ ቁጥር 144/2011 በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረት የታክስ ስሌት የሚሻሻልባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-
ታክስ ከፋዩ ራሱ ያዘጋጀው የታክስ ስሌት እንዲሻሻል ሲያመለክት በሚከተሉት ምክንያቶች ሚኒስቴሩ ሊያሻሽልለት ይችላል፡፡
የድምር ስህተት ሲኖር፤

የአጻጻፍ ስህተት ሲኖር፤
ከሒሳብ መደብ አመራረጥ (chart of account) ጋር የተያያዘ ስህተት ሲኖር፤
የጆርናል ምዝገባ ስህተት ሲኖር፤
ሒሳብ ወደ ሌጀር ሲተላለፍ የተከሰተ ስህተት ሲያጋጥም፤

ከሒሳብ ማስተካከያ (adjusting entry) ጋር የተያያዘ ስህተት ሲያጋጥም፤
በሒሳብ መዝገብ ላይ ሳይመዘገብ የተዘለለ የገቢና ወጭ ሰነድ ሲኖር፤
የመጀመሪያ ወይም የመጨረሻ ሀብት ቆጠራ አያያዝ ስህተት ሲኖር፤
የሒሳብ አያያዝ ዘዴ ስህተት ሲያጋጥም፤

በታክስ ህጎች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርዱ የውጭ ኦዲተሮችን የኦዲት ሪፖርት ሲመረመር ባገኘው ግኝት መሰረት የሚደረግ ማስተካከያ ሲያጋጠም፤ ሶስተኛ ወገን በሚሰጠው ማረጋገጫ ወይም በፍርድ ቤት በሚሰጥ ውሳኔ መሰረት በሂሳብ መዝገቡ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ሲያስፈልግ፤
በታክስ ሕግ ያልተፈቀደ ወጭ በተቀናሽነት በመያዙ ምክንያት የተፈጠረ ስህተት ሲኖር



የግልና የንግድ ሒሳቦች በመቀላቀላቸው የተፈጠረ ስህተት ሲያጋጥም፤
በታክስ ማስታወቂያ ቅጽ ላይ የአመዘጋገብ ወይም የአገላለጽ ስህተት ሲያጋጥም፤

በታክስ ወይም በተለይ በኤክሳይዝ ታክስ ሒሳብ አያያዝ ላይ የማምረቻና አስተዳደራዊ ወጪዎች ተፋልሰውና ባልተገባ ቦታ ላይ ተመዝግበው ሲገኙ የታክስ ስሌት ሊሻሻል ይችላል፡፡

ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች የተለየ እና በሚከፈለው የታክስ መጠን ላይ ለውጥ ሊያስከትል የሚችል አሳማኝ ምክንያት ሲያጋጥም ስራ አስኪያጁ የራስ ታክስ ስሌት ማሻሻያ እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል፡፡

ምንጭ ፟ የገቢዎች ሚኒስቴር

Related Post