አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ከወጪ መጋራት ጋር ተያይዞ የአሰሪዎች ግዴታ

ከወጪ መጋራት ጋር ተያይዞ የአሰሪዎች ግዴታ
ከወጪ መጋራት ጋር ተያይዞ የአሰሪዎች ግዴታ

ከወጪ መጋራት ጋር ተያይዞ የአሰሪዎች ግዴታ ማንኛውም አሰሪ፡-

1. የቀጠራቸውን ተጠቃሚዎች ዝርዝር ለባለሥልጣኑ ወይም ለሚመወክለው የማስታወቅ
2. በገንዘብ ለመክፈል ግዴታ ከገቡ ተጠቃሚዎች የሚፈለግባቸውን እዳ የሚያሳይ ማስረጃ ከተጠቃሚዎቹ በመቀበልና ስለ ትክክለኛነቱ ከሚኒስቴሩ በማረጋገጥ በየወሩ ከጥቅል ደመወዛቸው ቢያንስ 10% እየቀነሰ ከእያንዳንዱ ወር መጨረሻ አንስቶ ባሉት ሰላሳ ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴሩ ወይም ለሚወክለው የመክፈል

3. ተጠቃሚዎች ከተቋሙ የተሰጣቸውንና የሚፈለግባቸውን እዳ የሚያሳየውን ማስረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ ካልሆኑ የጥቅል ደመወዛቸው አንድ ሶስተኛ እየቀነሰ ለሚኒስቴሩ ወይም ለሚወክለው ገቢ የማድረግ፣

4. ገንዘብ በመክፈልም ሆነ አገልግሎት በመስጠት እዳቸውን ከፍለው ያጠናቀቁ ተጠቃሚዎችን ዝርዝር ክፍያው በተጠናቀቀበት ወር ለሚኒስቴሩ ወይም ለሚወክለው የማሳወቅ

5. አገልግሎት በመስጠት እንደሚከፍሉ ተገልጾ የተመደቡለትን ተጠቃሚዎች ተገቢውን ክትትል በማድረግ ማሰራትና አገልግሎት ካቋረጡ ሙሉ ለሙሉ ማቋረጣቸውን በማረጋገጥ ወዲያውኑ ለሚኒስቴሩ፣ ለትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ለመደባቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የማሳወቅ ግዴታ አለበት ፡፡

(ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር)

Related Post