አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ አይነትና ምንነት

ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ አይነትና ምንነት
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ አይነትና ምንነት

አንድ የተቀጠረ ሰራተኛ ካለፈው፣ አሁን ካለው ወይም ወደፊት ከሚመጣው የቅጥር ውል ጋር በተያያዘ የሚያገኘው ደመወዝ/ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ዋጋ ክፍያ፣ ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብ ወይም የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት፣ በዳኝነት ውሳኔ መሠረት በጥሬ ገንዘብ (በዓይነት) የተቀበለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ከታክስ ነጻ ከተደረገው ውጭ እንደ ገቢ ተቆጥሮ ታክስ የሚሰላበት ይሆናል፡፡

አንድ ተቀጣሪ ከመቀጠር የሚያገኘው ገቢ በኢትዮጵያ የመነጨ ነው የሚባለው፡-
– ክፍያው የሚፈፀመው ስፍራ ግምት ውስጥ ሳይገባ ኢትዮጵያ ውሰጥ ከሚከናወነው የቅጥር አገልግሎት የተገኘ ገቢ ወይም
– የቅጥር አገልግሎቱ የትም ቢከናወን በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ስም ክፍያው ለተቀጣሪው ከተፈፀመ ነው፡፡



– ተቀጣሪው ከመቀጠር በሚያገኘው ገቢ የሚያወጣው ማንኛውም ወጪ በተቀናሽ ሊያዝለት አይችልም፡፡
– ማንኛውም ቀጣሪ ተቀጣሪው መክፈል የሚኖርበትን ግብር ከተቀጣሪው ገቢ ላይ ሳይቀንስ ራሱ ለተቀጣሪው በሙሉ ወይም በከፊል የከፈለለት እንደሆነ፣ በቀጣሪው የተከፈለው የግብር መጠን ተቀጣሪው ከመቀጠር ከሚያገኘው ግብር በሚከፈልበት የገንዘብ መጠን ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል፡፡

(ምንጭ- የገቢዎች ሚኒስቴር የካቲት 11/2014)

Related Post