አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

ኢንተርኔት ለኢትዮጵያዉያን ሠፊ የሥራ እድል ይፈጥራል

ኢንተርኔት ለኢትዮጵያዉያን ሠፊ የሥራ እድል ይፈጥራል
ኢንተርኔት ለኢትዮጵያዉያን ሠፊ የሥራ እድል ይፈጥራል

አፍሪኮም ከተሰማራባችዉ የተለያዩ የስራ ዘርፎች አንዱ ቢዝነስ ፕሮሰሲንግ አዉሶርሲንግ ዋነኛዉ ነው።ቢዝነስ ፕሮሰሲንግ አዉትሶርሲንግ ማለት የአንድን ድርጅት ስራ ሌላ ድርጅት ተረክቦ ሲሰራ ማለት ነዉ። ቢዝነስ ፕሮሰሲንግ አዉትሶርሲንግ በሃገራችን ላይ ለመስራት አፍሪኮም ግንባር ቀደም ሲሆን ለወጣቶች በዚህ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትልቅ የስራ እድልን እንዳለ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሞያ ይናገራሉ።

ይህን የሚያደርጉት ድርጅቶች ወጪ ለመቀነስ፣ አለም አቀፍ የሆነ ንግድ ለመስራት እንዲሁም ይበልጥ ዉጤታማ ለመሆን ነዉ። በሌላም በኩል አፍሪኮም በሀገር ዉስጥ የተለያዩ ድርጅቶችን በወረቀት ፋይል ይቀመጡ የነበረዉን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የወረቀት ስራን ማስቀረት ችሎአል። በተጨማሪም ለድርጅቶች ከዘመኑ ጋር ማስኬድ የሚያስችላቸዉን ቴክኖሎጂን በመቅረተፅ ትልቅ አስተዋጾ እያረገ ይገኛል።

በህንድ ውስጥ ከሚገኙት ድርጅቶች 75% የሚገኙት በተለያዩ የሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ 43% ቢዝነስ ፕሮሰሲንግ አዉትሶርሲንግ ላይ የሚሰሩ ናቸዉ፣ እነዚህ ድርጅቶች ከሌሎቹ ሲነፃፀሩ የ20% የገቢ እድገት አላቸዉ ፣ በሀገራችንም የኢንተርኔት መስፋፋት እና ምሩቅ ተማሪዎች ብዛትን በመጠቀም ከዚህ የስራ እድል ተጠቃሚ የመሆን አቅም አላት።

Related Post