አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ስለ ኢ-ታክስ በጥቂቱ

ስለ ኢ-ታክስ በጥቂቱ
ስለ ኢ-ታክስ በጥቂቱ

ኢታክስ ምንድነው? ኢንተርኔትን በመጠቀም ታክስን የማስታወቅ፣ ክፍያን የመፈፀም፣ የክሊራንስ አገልግሎት የማግኘት እና የታክስ ነክ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎች ለማግኘት የሚረዳ አሰራር ነው፡፡

ለግብር ከፋዩ ምን ጠቀሜታ አለው?
በተለይም በአሁኑ ወቅት የኮሮና ወረረሽኝ ለመከላከል ሚመከረው አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳ ነው፡፡ ከማኑዋል አሰራር የተለየ በመሆኑ እና ግብር ከፋዮች ግብር ለመክፈል የግብር መክፈያ ጣቢያ በአካል መምጣት ስለማይጠበቅባቸው ለእንቅስቃሴ ያስፈልግ የነበረውን የትራንስፖርት/ የነዳጅ ወጪን እና ሰነዶችን ኮፒ ለማድረግ የሚያስፈልግን ወጪ በማስቀረት እና ጊዜ በመቆጠብ በንግድ ስራ ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል፡፡ ወረፋ እና የስራ ሰዓት መጠበቅ ሳይስፈልጋቸው ሳምንቱን ሙሉ በየትኛውም ሰዓት ግብራቸውን አሳውቀው ለመክፈል ያስችላቸዋል፡፡

አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
ለበርካታ ግብር ከፋዮች በአጠቃቀሙ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷቸው አዲስ አበባ በሚገኙ በአራቱም የፌዴራል ግብር መክፈያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየተሰጠ ነው፡፡

ኢ-ታክስ ምን ዓይነት አገልግሎት የሚያጠቃልል ነው?
ኢ-ፋይሊንግ፡- ግብርን ለማሳወቅ የሚረዳ በኢታክስ ውስጥ የሚጠቃለል አሰራር ነው፡፡ ኢ-ፔይመንት፡- ባሳውቁት ግብር መሰረት ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችል ነው፡፡

ኢ-ክሊራንስ፡– ለንግድ ስራቸው ክሊራንስ ለሚፈልጉ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክ መንገድ የክሊራንስ አገልግሎት የሚሰጥበት ነው፡፡ አገልግሎቱን ያልጀመሩ እንዴት መጀመር ይችላሉ? ቀላል ነው፡፡ ግብር በሚከፍሉበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኙ የግብር ከፋዮች ትምህርት የስራ ሂደት ማብራሪያ በመጠየቅ አገልግሎቱን እንዲጀምሩ ድጋፍ ይደረግልዎታል፡፡

ምን ያህል አስተማማኝ ነው?
ከክፍያ ጋር በተያያዘ እርስዎ ሳያዙ ከሂሳብዎ ምን ዓይነት ገንዘብ ተቀናሽ የማይደረግ ሲሆን በዚህ ስርዓት ግብርዎን ሲከፍሉ (ኢፔይመንት የምንለው) ስለመክፈልዎ ማረጋገጫ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ይላክልዎታል፡፡

የክፍያ አማራጮች አሉ?
አዎ፡፡ የኢፔይመንት የክፍያ አማራጮች በኢንተርኔት ባንኪግ ሲስተም በሞባይል መተግበሪያና በዩኤስኤስዲ ሲስተም እንዲሁም በባንኮች ቅርንጫፍ (በኮር ባንኪንግ ሲስተም) መፈፀም የሚያስችል ነው፡

Related Post