አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ስለኪራይ ገቢ ግብር

ስለኪራይ ገቢ ግብር
ስለኪራይ ገቢ ግብር

ብዙ ነገሮችን ልናከራይ ወይንም ልንከራይ እንችላለ በዚሁ መሰረት ቤት ብቻ ሳይሆን ቁሳቁስና ሌሎች ነገሮችም የሚከራዩ እና የኪራይ ገቢ የሚከፈልባቸው ቢሆንም ለዛሬ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢን በተመለከተ የሚከተለውን እንበላችሁ፡፡

ከኪራይ ገቢ ላይ ግብር የሚከፈለው በግብር ዓመቱ ግብር ከፋዩ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ ከሚቀረው ገቢ ላይ ነው፡፡

ቤት ወይም ህንጻ በማከራየት የሚገኝ ጠቅላላ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-
1. የኪራይ ዋጋ ጭማሪን ወይም ተመሳሳይ ክፍያዎችን ጨምሮ በኪራይ ወሉ መሠረት ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የሚያገኘው ማናቸውም የገንዘብ መጠን፣

2. በኪራይ ውሉ መሠረት ተከራይ አከራዩን በመወከል በግብር ዓመቱ ለሌሎች የሚከፍላቸው ክፍያዎች፣

3. በቤቱ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ማስተካከያ ይሆን ዘንድ ግብር ከፋዩ የያዘውና በግብር ዓመቱ ያልተጠቀመበት ለግብር ከፋዩ ገቢ የተደረገው ማናቸውም ቦንድ፣ ዋስትና ወይም ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን፣

4. ለግብር ከፋዩ ከሚከፈለው ኪራይ በተጨማሪ በኪራይ ውል መሠረት ተከራይ ራሱ ለቤቱ እድሳት ወይም ማሻሻያ የሚያወጣው ገንዘብ፣

5. ግብር ከፋዩ ቤቱን ያከራየው ከዕቃዎች ጋር በሚሆንበት ጊዜ ያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከዕቃዎቹ የተገኘውን የኪራይ ገቢም ያጠቃልላል፡፡

የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ግብር ከፋይ በግብር ዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ ገቢውን ለማግኘት የወጣና በግብር ከፋዩ የተከፈለ አስፈላጊ የሆነ ወጪ ተቀናሽ የሚደረግ ሲሆን ይህም ወጪ የሚከተሉትን ይጨምራል፡

1. ቤቱ ያረፈበት የመሬት ኪራይ (lease)፣
2. የጥገና ወጪ፣
3. የቤቱ፣ የቤት ዕቃዎችና የመሣሪያዎች የእርጅና ቅናሽ፣
4. ወለድና የመድን አረቦን፣
5. ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ለመንግስት ወይም ለከተማ አስተዳደር የከፈላቸው ክፍያዎች፣

ምንጭ- የገቢዎች ሚኒስቴር

Related Post