አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ለከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ተጓዦች

ለከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ተጓዦች
ለከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ተጓዦች

ለከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ተጓዥ ኢትዮጵያዊያን ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከየኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ‹‹ታላቁ የኢድ ሶላት በኢትጵያ›› በሚል ባስተላለፉት ጥሪ ዲያስፖራው በሀገር ቤት እንዲያሳልፉ እና የጎረቤት ሀገራትና የኢትጵያ ወዳጆች ጥሪውን እንዲቀላቀሉ ሀገራዊ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

በዚህ መነሻ ጥሪ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ አካል የሆነው ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት በሚል ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው ለሚመጡ ከቪዛ፤ ፓስፖርት እና ከትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ዓላማው እንዲሆን ለማስቻል ጊዚያዊ አሰራር ማውጣት በማስፈለጉ ይህንንም በውጭ ያሉ ኤምባሲዎች በመገንዘብ በውጭ ያሉ ዲያስፖራዎች ለሚጠይቁና ለሚያነሱት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መሰጠት እንዲቻልና ሂደቱን እንዲያሳልጥ ጊዚያዊ መመሪያው ከሚያዚያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጸድቆ ከወጣበት ጀምሮ ስራ ላይ ዉሏል። ይህም፡-

1. ፓስፖርትና የትውልድ መታወቂያ ጋር በተያያዘ .
 አዲስም ሆነ እድሳት የፓስፖርት አገልግሎት በኦንላየን የሚሰጥ በመሆኑ በኦንላየን ያመለከቱ ግለሰቦች ከ15 ቀን ባነሰ ታትሞ የሚደርሳቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም ያልደረሳቸው ካሉ ኤምባሲው አይዲ ቁጥር ከላከልን በአስቸኳይ ታትሞ የሚላክ ይሆናል።
 የጉዞ ሠነድ (Travel document) ሳይዙ ጉዞ ማድረግ የማይቻል መሆኑ

2. ከቪዛ ጋር በተያያዘ
 ትውልደ ኢትጵያዊ ሆኖ የታደሰም ሆነ የአገልግሎት ጊዜው ያለፈበት የትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ ያላቸው ያለቪዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባት የሚችሉ ሲሆን ጊዜው ያለፈበትም ይሁን ያላለፈበት የትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ በእጃቸው መያዝ ይኖርባቸዋል፤

 በተለያየ ምክንያት ጥገኝነት የጠየቁ እና የሌላ አገር ሰነድ ይዘው ለሚመጡ /exept Ethiopia/ መንገደኞች ከኤምባሲው የተጻፈላቸውን የማረጋገጫ ደብዳቤ በማየት እዚያው ደብዳቤ ላይ የገቢ ማህተም ተመቶ በመዳረሻ እንዲገቡ ይደረጋል። ኤምባሲው በአቅራቢያ የሌላቸው መጥተው በመዳረሻ በተዘጋጀው ካርድ ላይ ገቢ ማህተም ተመትቶላቸው መግባት ይችላሉ።

የኤርትራ ፓስፖርት የያዙትም ሆነ የውጭ ዜግነት ትራቨል ዶክመንት ያለቸው ኤርትራዊያን በልዩ ሁኔታ በኦንላየን ወይም በመዳረሻ ቪዛ ይሰተናገዳሉ፤

 በተለያዩ ዓለማት የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በአሉን በጋራ ለማክበር ፍላጎት ያላቸው በኤምባሲ የተረጋገጠ ደብዳቤ ከያዙ ብቻ በመዳረሻ ላይ ቪዛ ማግኘት ይችላሉ፤

 በጎረቤት ሀገራት የሚገኙ የውጭ ዜጎች በባቡር ወይም በየብስ ኬላዎች የኦንላየን ቪዛ ይዘው ለመግባት የሚመጡ በተቀላጠፈ መልኩ አገልግሎቱ በየብስ የኢሚግሬሽን መቆጣጠሪያ ኬላ ይሰጣል፤

 በዓሉን ለመታደም የሚመጡ የሌላ እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያውያንም ሆኑ የሌላ ሀገር ዜጎች በተመሳሳይ መልኩ አገልግሎቱን በላይ በየቀመጠው አቅጣጫ መሰረት አገልግሎቱን ያገኛሉ።

Related Post