አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

230 ህገ-ወጥ የቱርክ ሽጉጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

230 ህገ-ወጥ የቱርክ ሽጉጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
230 ህገ-ወጥ የቱርክ ሽጉጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ባህር ዳር ጉምሩክ ሰራባ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ኬላ ላይ በቀን 16/9/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 በተደረገው ፍተሻ ብዛቱ 230 የቱርክ ሽጉጥ በኒሳን ፖትሮል ተሸከርካሪ በሻግ ውስጥ ጭኖ ከሸዲ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ ተያዘ፡፡

በተጨማሪ በተጠቀሰው ቀን ከሰዓት በኃላ ደግሞ ብዛቱ 300 የሆነ የቱርክ ሽጉጥ ጥይት በህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ውስጥ በመደበቅ ከገንደውሃ ወደ ጎንደር በመጓዝ ላይ እያለ በሰራባ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

በዋጋ የማይተመነውን የሰው ህይወት ሊቀጥፍ የሚችል የጦር መሣሪያ በህገ ወጥ መንገድ ወደ መሀል አገር እንዲሁም ከቦታ ቦታ ሲዘዋዋር የነበረ የጉምሩክ ሠራተኞችና ፀጥታ አካላት በትብብር በሰሩት ስራ ህገ-ወጥ የቱርክ ሽጉጥና የተለያዩ ዓይነት ጥይቶች በግልና በህዝብ መመላለሻ ተሸከርካሪ ውስጥ ደብቆ ለማለፍ ሲሞክሩ ከሁለት ተጠሪጣሪ ግለሰቦዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የህዝቡን ደህንነት ሰጋት ላይ የሚጥሉ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች በተለያየ ጊዜ በጉምሩክ ኬላ ጣቢያ በአዘዋዋሪዎች እጅ እየተያዙ በመሆኑ በቀጣይበትም የኮንትሮባንዲስቶች እና ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪችን እንቅስቃሴ ለማጋለጥ በሁሉም መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ቁጥጥር የሚናደርግ ሲሆን ህብረተሰቡም እንደተለመደው ሁሉ አስፈላጊውን ጥቆማ በመስጠት በጎናችን እንዲቆም ሀገራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

Related Post