አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

1028 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

1028 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ
1028 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

ትላንት ረቡእ ኢለት በተደረጉ ሦስት በረራዎች ከሳዑዲ አረቢያ 1፣028 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የማስመለሱ ጥረት ተጠናክረው የቀጠለ ሲሆን፥ ዛሬ በተደረጉ ሦስት በረራዎችም 1 ሺህ 28 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ከተመላሾች መካከል አምስቱ ህጻናት ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወንዶች ናቸው።

አዲስ አበባ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል። መንግሥት በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና 16 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን በአባልነት ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ሃገር ለመመለስ በማቀድ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል ።

Related Post