አርእስተ ዜና
Sun. Jan 26th, 2025

ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራን የኢነርጅ ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ ነው

ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራን የኢነርጅ ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ ነው
ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራን የኢነርጅ ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ ነው

ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራን አማራጭ የኢነርጅ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግል ለማድረግ እየተሰራ ነው።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ሴክተር ሪፎርም ፐርፎስማንስ ፕሮጀክት ደን በመቁረጥ ለቦይለር በሃይል ምንጭነት እንጨትን የሚጠቀሙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ የተባለውን መጤ አረም ፈጭቶ ወደ ብሪኬት በመቀየር የደን ጭፍጨፋን ለማስቀረት የሚያስችል የኃይል አቅርቦት ቴክኖሎጅ ላይ የሙከራ ስራ እየሠራ መሆኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዳዊት አለሙ በምስራቅ አፍሪካ የአርብቶ አደሮች ኤክስፖ ላይ የሴክተሩን ፖቪሊዮኑን ለጎበኙ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች አስረድተዋል ።

ሙከራው መጤ አረሙን በመፍጨት ለስሚንቶ አምራቾች ለኃይል ምንጭነት ከማዋል ባሻገር ቦይለር ያላቸው ና የደን ውጤቶችን በኃይል ምንጭነት ለሚጠቀሙ አምራቾች እንደ አማራጭ የኢነርጅ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግል በማድረግ በደን ጭፍጨፋ ምክንያት የሚዛባውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቀነስ እንደሚያስችል አቶ ዳዊት ገልፀዋል። የሙከራ ትግበራው ወደ ስራ ሲገባ ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

Related Post