አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሱዳኑ አቻቸው ጋር በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሱዳኑ አቻቸው ጋር በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሱዳኑ አቻቸው ጋር በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸው፣ ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያልተቋጩ ጉዳዮችን ለማጠናቀቅ እና የተዛባ ግንዛቤ የነበረባቸውን ጉዳዮች ለማጥራት የታለመ ነው ተብሏል።

የአካባቢ ጥበቃ፣ የግድቡ የደኅንነት ሁኔታ እና የመረጃ ልውውጥን ስለ ማመቻቸት፣ በሱዳን በኩል ለተነሡት ጉዳዮች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወቅታዊ የሥራ ክንውኑ ያለበትን ደረጃ ገልጸዋል። አክለውም፣ የሕዳሴው ግድብ ለሦስቱ የተፋሰሱ ሀገራት ኢኮኖሚ መጠናከር ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የቴክኒክ ውይይቱን በሁለቱ ሀገራት የውኃ ሚኒስትሮች አማካኝነት ለመቀጠል ስምምነት ላይ መደረሱም ተገልጿል።

Related Post