አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ዳግም ኬኔዲ ጀነራል ትሬዲንግ ስምምነት ፈጸሙ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ዳግም ኬኔዲ ጀነራል ትሬዲንግ ስምምነት ፈጸሙ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ዳግም ኬኔዲ ጀነራል ትሬዲንግ ስምምነት ፈጸሙ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከዳግም ኬኔዲ ጀነራል ትሬዲንግ ጋር የስራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በዚህ ሳምንት አከናወነ።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በግብርና እንዲሁም በግብርና ነክ ኢንዱስትሪ የስራ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ደንበኞቹ ‹‹ለአምራቹ›› በተሰኘው አዲስ የባንክ አገልግሎቱ ከዳግም ኬኔዲ ጄነራል ትሬዲንግ ጋር በተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ መሰረት በሃገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪ ጊዜ ‹‹ሚዛን›› በሚል ሃገርኛ ስያሜ የተሰየሙትን የእርሻ ትራክተሮች በካፒታል ሆቴል በተከናወነ ደማቅ ፕሮግራም ለዕይታ ቀርበው ተመርቀዋል ፡፡

ዳግም ኬኔዲ ጀነራል ትሬዲንግ ሁለገቡን አርቲስትና የሚድያ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ የሾመ ሲሆን አርቲስቱም ገበሬውን ወደ ከፍተኛ አምራችነት የሚወስደውን ‹‹ ሚዛን ›› ትራክተር ለማስተዋወቅ በመመረጤ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል ያለ ሲሆን ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አርሶ አደሩን ለመርዳት የጀመረውን ‹‹ ለአምራቹ›› የባንክ አገልግሎትም ለአርሶ አደሩ እጅግ ከፍተና ጠቀሜታ አለው ሲልም ገልጿል ፡፡

Related Post