አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ጀነሬሽን አንሊሚትድ የወጣቶች ውድድር 2014 ሁለት አሸናፊ ቡድኖችን መረጠ

ጀነሬሽን አንሊሚትድ የወጣቶች ውድድር 2014 ሁለት አሸናፊ ቡድኖችን መረጠ
ጀነሬሽን አንሊሚትድ የወጣቶች ውድድር 2014 ሁለት አሸናፊ ቡድኖችን መረጠ

ጀነሬሽን አንሊሚትድ የወጣቶች ውድድር 2014 በዩኒሴፍ የተጀመረ አለም አቀፍ ሥራ ሲሆን 2 አሸናፊ ቡድኖችን ኒውዮርክ እሜሪካ ለሚካሄደው አለም አቀፉ የወጣቶች ውድድር በመምረጥ ዛሬ ተጠናቋል፡፡

እነዚህ 2 ቡድኖች የንግድ ሃሳባቸውን ነሐሴ መጨረሻ ላይ ለአለም አቀፉ ውድድር የሚያቀርቡ ሲሆን ቡድኖቹ የተመረጡት እያንዳንዳቸው 100,000 ብር ከተቀበሉት የመጨረሻዎቹ 5 ቡድኖች መካከል ነው፡፡ በመዝጊያ ሥነ-ስርዓቱ ላይ አምስቱ ቡድኖች በአካባቢያቸው ያሉ የተለያዩ ችግሮችን የሚቀርፉ የንግድ ሃሳቦቻቸውን አቅረበዋል፡፡ የንግድ ሃሳቦቹ በመኖ ምርት ፣ በውሃ ማጣራት ፣ በባህላዊ (የኢትዮጵያ) ልብሶች አምራች ማሽን ፣ በፕሮግራሚንግ/ኮዲንግ እና በመተንፈሻ አጋዥ ማሽን ዙሪያ ያጤነጠኑ ናቸው፡፡

የአሸናፊ ቡድኖች የመፍትሔ አምጪ የንግድ ሃሳቦች ከሌሎች የንግድ ሃሳቦች ጋር በመሆን በአለም አቀፉ የዳኝነት ሂደት ላይ ይቀርባሉ፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች ከተመረጡ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡ በተጨማሪም ብቁ እንዲሆኑ በጀነሬሽን አንሊሚትድ አጋሮች ከተዘጋጀ የአለም አቀፍ የማሳደጊያ ፕሮግራም ድጋፍ ያገኛሉ፡፡

በሥራና እና ክህሎት ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጥዑመእግዚ ፈቃዱ በመዝጊያው ሥነ-ስርዓት ላይ ,‹‹እንደ ሀገር ብዙ ችግሮች አሉብን ነገር ግን ብዙ እድሎችም አሉን፡፡ ይህ ውድድር ወጣቱ በችግሮቹ እና በእድሎቹ መካከል ድልድይ እንዲሰራ እድልን ያመቻችለታል፡፡ በዚህም ምክንያት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሁልጊዜ ማኅበረሰባዊ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ እና ችግሮችን የሚፈቱ የንግድ ሃሳቦችን ይደግፋል፡፡ ሀገራችን ብዙ ችግሮች ስላሉባት ሁሉንም የሥራ ፈጠራ ሃሳቦች ጠቃሚ መሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡ ስለዚህ ተመሳሳይ ውድድሮችን እና መድረኮችን ማዘጋጀት እና መደገፍ እንቀጥላለን፡፡››

ጀነሬሽን አንሊሚትድ ከወጣቶች ጋር ሆኖ ለወጣቶች የሚሰራ ቀውስን ወደ እድል የሚቀይር በዓለም ፈር ቀዳጅ የመንግስት- የግል አካላትና – የወጣቶች ጥምረት (PPYP) ነው፡፡ ውድድሩ በአለም ዙሪያ ከ35 በሚበልጡ ሀገራት ውስጥ ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ዘላቂ የልማት ግቦች(SDGs) በኢትዮጵያ የሚኖራቸውን ስኬታማነት የሚያፈጥኑ መፍትሄ አምጪ የፈጠራ ሃሳቦቻቸውን ንድፍ እንዲያቀርቡና ሃሳቦቻቸውን ወደ እውነታ ለመቀየር ወጣቶች ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ ያደርጋል ፤ የቅርብ ድጋፍና ክትትል(ሜንተሪንግ) ይሰጣል፤ ሃሳባቸውን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችላቸውን መነሻ ገንዘብ ይመድባል፡፡ የጀነሬሽን አንሊሚትድ እና የወጣቶች ውድድር 2014 ትኩረት ወጣቶችን በክህሎት ማስታጠቅ፤ ወጣቶችን ከፈጠራ ሥራ ጋር እና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ከሚያመጡ እድሎች ጋር ማገናኘት ነው፡፡

የመጀመሪያው ዙር ውድድር በኢትዮጵያ ውስጥ በ5 ከተሞች፡- አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ሀዋሳና ጅግጅጋ ላይ ለ10 ሳምንታት እስከ መጋቢት 30 2014 ተካሂዷል፡፡

ከ700 በላይ ቡድኖች ለጄኒዩ የወጣቶች ውድድር 2014 ያመለከቱ ሲሆን 364 የመጀመሪያውን የምርጫ ሂደት አልፈው ነበር፡፡ ከጥልቅ ግምገማ እና ቃለ-መጠይቆች በኋላ 10 ቡድኖች ቁልፍ የሕይወት ክህሎቻቸውን የሚያሳድጉባቸውን እና ቁልፍ የሥራ ፈጠራ ክህሎቶቻቸውን የሚያበስሉባቸውን መንገዶች እንደዚሁም ስኬታማ ንግድ መምራት እና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች መሆን የሚያስችሏቸውን መንገዶች ለመማር የክህሎት ማዳበሪያ ውሎና አዳር ያካተተ የስልጠና ጊዜያትን ተቀላቅለዋል፡፡ በአእምሮ ውቅር ለውጥ እና በአመራር ላይም ስልጠና ወስደዋል፡፡ የክህሎት ማዳበሪያ ውሎና አዳር ያካተተ የስልጠና ጊዜያቱ የተካሄደው ለአስር ተከታታይ ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ በሥራ አመራር ኢኒስትቲዩት እና በኢየሩሳሌም የልጆች እና የማኅበረሰብ ልማት ድርጅት(ጄክዶ) ነበር፡፡ የክህሎት ማዳበሪያ ውሎና አዳር ያካተተ የስልጠና ጊዜያቱ እንደተጠናቀቁ 10 ቡድኖች የንግድ ሃሳቦቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ዳኞች 5 የመጨረሻ ቡድኖችን መርጠዋል፡፡ እነዚህም ቡድኖች የሥራ ማስጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ አግኝተዋል ፤ ተጨማሪ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ(ሜንተሪንግ) ተደርጎላቸዋል ፤ የትስስር ጊዜም ተመቻችቶላቸዋል፡፡

የቅርብ ክትትልና ድጋፍ(ሜንተሪንግ) ሂደቱም ለአራት ሳምንታት ቆይቷል፡፡ እያንዳንዱ የቅርብ ተከታታይ እና ደጋፊ(ሜንተር) የተሰጠው/ጣት አንድ ቡድን ነበር፡፡ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ(ሜንተሪንግ) ክፍለ-ጊዜው በየሳምንቱ ለአንድ ወይም ለሁለት ሰዓት ተካሂዷል፡፡ ይዘቱም የንግድ ሃሳብ ትግበራን ፣ የገንዘብ ዝውውር እቅድን ፣ የሂደት ክትትል እና ችግሮችን መፍታትን ፣ የሥራ ማስጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ አጠቃቀምን ፣ የገበያ እቅድን ፣ የድርጅት አስተዳደር እቅድን እና አመራርን ያካትታል፡፡

የትስስር ጊዜው የተካሄደው መጋቢት 30 2014 የክብር እንግዶች ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተወካዮች እናም በንግድ ሃሳቦቹ ላይ ኢንቨስት ማድረግ አቅም ያላቸው ባለሀብቶች በተገኙበት የመዝጊያው ሥነ-ስርዓት ካበቃ በኋላ ነው፡፡ የትስስሩ ጊዜ ግብ ወጣቶቹ ሃሳባቸው የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ሊያግዟቸው ከሚችሉ ሰዎች ጋር ግኑኝነቶችን እንዲያዳብሩ ማገዝ ነው፡፡

ውድድሩ በኢትዮጵያ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የህጻናት ፈንድ (ዩኒሴፍ)፣ በተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ)፣ በዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጀት (አይ ኤል ኦ)፣ በተባበሩት መንግስታት ሥነ-ህዝብ ፈንድ (ዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ) እንዲሁም በሬዚደንት አስተባባሪ ቢሮ (አር ሲ ኦ) ድጋፍ ይደረግለታል፡፡ ፈርስት ኮንሰልት ሥራውን ያከናውናል፡፡

Related Post