አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የ25.4 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እና የጦር መሳሪያዎች ተያዘ

የ25.4 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እና የጦር መሳሪያዎች ተያዘ
የ25.4 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እና የጦር መሳሪያዎች ተያዘ

ባለፉት አስር ቀናት ውስጥ (ከግንቦት 12-21/12 ዓ.ም) ከ25.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ የወጣላቸውና ግምታዊ ዋጋ ያልወጣላቸው የተለያዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ እቃዎች እና የጦር መሳሪያ በጉምሩክ ሠራተኞችና በፀረ-ኮንትሮባንድ ግብረ-ዓይል በጋራ በሰሩት ስራ በጉምሩክ ኬላ ጣቢያዎች ላይ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ በሀገር እድገት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ይታወቃል፡፡ በተለይ በሀገራችንና በአለም አቀፍ የተከሰተውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ሁሉም ካለው በመቀነስ ወገኑን እየደገፈ ባለበት በዚህ ክፉ ወቅት አንዳንድ ራስ ወዳድ ግለሰቦች ደግሞ ከዚህ ተቃራኒ በመቆም የሀገር ሀብት ለመስረቅ፣ የማህበረሰቡን ሠላም ለማደፍረስ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን በመዘዋወር ተጠምዷል፡፡

ይሁን እንጂ የኮሚሽኑ ሠራተኞችና የፀጥታ አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት በጋራ በተሰራው ስራ በተለያዩ የጉምሩክ ኬላ ጣቢያዎች ማለትም በአዋሽ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ሞያሌ፣ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ ጅማ፣ ሞጆ፣ ቦሌ አየር መንገድና በሌሎች ኬላ ጣቢዎች የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የተሸከርካሪ መለዋወጫ፣ በቱርስት ስም የገባ ተሽከርካሪ፣ የተለያዩ ዓይነት አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ጊዜው ያለፈበት ምግብና የምግብ ዓይነቶች፣ የተለያዩ ዓይነት የጦር መሣሪያ፣ ሲጋራና ሺሻ የተያዙ ሲሆን የቁም እንስሳት ደግሞ ጨለማን ተገን በማድረግ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጅቡቲ ለማሻገር በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ በተደረገው ከፍተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

እንዲሁም በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያና በሞጆ ተርምናል በኩል የሚገቡ እቃ ሰነድ በመሰወር ምክንያት ንግድ በመጭበርበር ላይ የሚጠመዱ በጣም ጥቂት ስግብግብ ግለሰቦች በኮሚሽኑ ሠራተኞች በተደረገው ፍተሻ ሊጭበረበር የነበረው ከ3 ሚሊየን ብር በላይ እንደገና ታክስና ግብር ለመንግስት እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በሁሉም ጉምሩክ ኬላ ጣቢያ የሚሰሩ ሠራተኞቻችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌተ ተቀን ለዝናብና ሙቀት እንዲሁም በኮንትሮባንዲስቶች ማስፈራሪያ ሳይበገሩ ራሳቸውን መሰዋዕት በማድረግ ከሁሉም ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በማገልገል ላይ ላሉ አካላት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ምስጋናውን እያቀረበ፣ ራሳቸሁንና ቤተሰቦቻቸሁን ከቫይረሱ በመጠበቅ የኮንትሮባንድ እቃዎችንና ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል ከህዝቡ ጋር በመሆን ጠንክራቹ እንድትሰሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Related Post