የገንዘብ ሚኒስቴር 42 የመስክ ተሸከርካሪዎችን ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደሮችና ለፌዴራል መስሪያ ቤቶች አስረከበ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር በ234.2 ሚሊዮን ብር ወጪ በአለም አቀፍ ጨረታ የገዛቸውን 42 ቶዮታ ሃርድ ቶፕ የመስክ ተሸከርካሪዎችን ለ12 ክልሎች፣ ለ2 ከተማ አስተዳደሮችና ለ4 የፌዴራል መስሪያ ቤቶች አሰረከበ፡፡
የተሸከርካሪዎቹ ግዢ የተፈጸመው ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በገንዘብ ሚኒስቴር ተግባራዊ በሚደረገው በESPES-IPF ፕሮግራም በጀት ሲሆን የገንዘብ ሚኒስቴርን በመወከል ተሸከርካሪዎቹን ለተጠቃሚዎቹ ያስረከቡት በሚኒስቴሩ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዲቪዥን ሃላፊ አቶ ጋዲሳ አዳነ ናቸው፡፡
በቀጣይነትም የክልሎችን፣ የከተማ አስተዳደሮችንና የፌዴራል መስሪያ ቤቶችን የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት በ171 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገዙ 305 ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ 305 ዩፒ.ኤሶች፣ 220 ፕሪንተሮች ፣ 95 ጄኔሬተሮች እና 95 ወርክ ስቴሽን ኮምፒዩተሮች በሚቀጥሉት አስራ አምስት ቀናት ወስጥ ርክክብ እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡