አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የዉጭ ኩባንያ በኢትዮጵያ አዲስ የራይድ ትራንስፖርት ሊጀምር ነው

የዉጭ ኩባንያ በኢትዮጵያ አዲስ የራይድ ትራንስፖርት ሊጀምር ነው
የዉጭ ኩባንያ በኢትዮጵያ አዲስ የራይድ ትራንስፖርት ሊጀምር ነው

ያንጎ የተሰኘው አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በአዲስ አበባ የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ከተቋቋመው ‘ሹፌር’ ጋር አጋርነት መመስረቱን አስታወቀ።

በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት የሀገር ውስጥ የአይቲ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ጂ2ጂ በኢትዮጵያ የያንጎ ኩባንያ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ የፍራንቻይዝ ባለቤት በመሆን ኢትዮጵያን የያንጎ አገልግሎት ተደራሽ የሚሆባት 13ኛዋ የአፍሪካ ሀገር ያደርጋታል።

“ከጂ 2ጂ አይቲ ግሩፕ ጋር አጋርነት መስርተን ያንጎን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣታችን እጅግ በጣም ደስተኞች ነን" ሲሉ የያንጎ አፍሪካ ኃላፊ የሆኑት አዴኒዪ አዴባዮ ተናግረዋል። አክለውም "የያንጎ ቴክኖሎጂን የበለፀገ እውቀት እና አለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን በሀገር ውስጥ እውቀት እና በኢትዮጵያ ገበያ ግንዛቤ የካበተ ልምድ ካለው ሹፊር ጋር በማጣመር ለኢትዮጵያ ህዝብ ልዩ የሆነ የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደምንሰጥ ባለሙሉ እምነት ነን።”

“የጋራ እይታችን እና እውቀታችን ኢንዱስትሪውን የሚቀይር የላቀ፣ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችለን እናምናለን። ይህም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ ከማበርከቱ ባሻገር ለኢትዮጵያ የትራንስፖርት ችግር አዲስ የመፍትሄ ምዕራፍ መጀመሩን ያመላክታል። በመሆኑም በዚህ አጋርነት አማካኝነት ይህን የላቀ አገልግሎት ለህብረተሰባችን በማድረሳችን ደስተኞች ነን” በማለት የጂ2ጂ ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር ቴዎድሮስ መሃሪ ተናግረዋል።

ያንጎ ሞባይል መተግበሪያ ለአይኦኤስ እና አንድሮይድ ስልኮች በአማርኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን መተግበሪያውን በነፃ ማውረድ ይቻላል። መኪና ለማዘዝ የሚፈልጉ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን በማውረድ ከከፈቱ በኋላ በቀላሉ የት መሄድ እንደሚፈልጉ ሲገልጹ የአካባቢ ጠቋሚ አገልግሎቱ ያሉበትን ቦታ በመጠቆም በአቅራቢያው ያለ አሽከርካሪ በፍጥነት በቦታው እንዲደርስ ያደርጋል።

አገልግሎቱ ለጊዜው ለተጠቃሚዎች የሚሰጠው የክፍያ አማራጩ በጥሬ ገንዘብ ብቻ የሚሰራ ሲሆን በዚህም መሰረት አንድ ተጠቃሚ መኪና አዞ የመድረሻ አድራሻውን ሲያስገባ የሚሰላውን የጉዞ ዋጋ አይቶ ማረጋገጥ ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ክፍያውን እንደ ቴሌብር እና መሰል የሀገር ውስጥ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ጋር በከፊል ኣለማቀናጀት አቅዷል።

በሌላ በኩል አንድ ተጠቃሚ ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገው፣ ጥያቄ ካለው፣ ወይም በተሳፈረበት መኪና ውስጥ የረሳው ነገር ካለ ጥያቄዎቹን የሚመልሱለትን የደንበኛ አገልግሎት ማዕከል በመተግበሪያው በኩል ማግኘት ይችላሉ። ለተጨማሪ የጥራት ቁጥጥር ዘዴ ተጠቃሚዎች ለእያንዳንዱ ጉዟቸው ደረጃ እንዲሰጡ መተግበሪያው የሚያስችላቸው ሲሆን፣ በተጠቃሚዎች ዝቅተኛ ደረጃ የሚሰጣቸው አሽከርካሪዎች ለተወሰነ ጊዜ አገልግሎቱን እንዳይሰጡ ሊታገዱ ይችላሉ።

ያንጎ ዓለም አቀፍ ቴክኖሎጅዎችን ወደ ዕለታዊ አገልግሎቶች የሚቀይር የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው። ለፈጠራ በማያወላውል ቁርጠኝነት፣ በአለም ዙሪያ መሪ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተለያዩ ክልሎች ያለምንም እንከን ወደ የተቀናጀ ዕለታዊ አገልግሎቶች እንቀይራለን እንዲሁም እናሳድጋለን። የያንጎ የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት መተግበሪያ በአይቮሪ ኮስት ፣ ጋና ፣ ካሜሩን ፣ ሴኔጋል ፣ ዛምቢያ ፣ አንጎላ ፣ ኮንጎ ብራዛቪል ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሞዛምቢክ ፣ አልጄሪያ እና ሞሮኮን ጨምሮ በአውሮፓ ፣ መካከለኛው እስያ ፣ ደቡብ አሜሪካ ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ውስጥ ባሉ በርካታ ሀገሮች ውስጥ አገልግሎቱን ተደራሽ አድርጓል።

በ2016 የህብረት ኩባንያ ሆኖ የተመሰረተው ጂ2ጂ አይቲ ግሩፕ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ዓለም አቀፍ ልምድ ባላቸው ቡድን የተደራጀ ኩባንያ ነው። ኩባንያው ዋና ትኩረቱ አራት ቁልፍ ስትራቴጂካዊ የገበያ ቦታዎችን የሚያጠቃልል ሲሆን እነዚህም እንደ ኤስኤምኤስ፣ አይኤስፒ፣ ኢቪዲ ያሉ የቴሌኮም እሴት አገልግሎቶች፣ የአይቲ መሠረተ ልማት፣ የደህንነት፥ እንዱሁም የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልጎልቶችን ያጠቃልላሉ። እንደ ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ፣ኔትወርክ ኢንጂነሪንግ፣ቴሌኮም አገልግሎት እና የትራንስፖርት አገልግሎት መሰል ዘርፎች ላይ ከ40 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው የጂ2ጂ አይቲ ቡድን
በኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) ዘርፍ ትልቅ ቦታ ይይዛል።

ጂ2ጂ በአካባቢው ካሉ ሌሎች የአይቲ ኩባንያዎች የሚለየው ለደንበኞቹ የረጅም ጊዜ አጋር ለመሆን ባለው ቁርጠኝነት ነው። ጂ2ጂ መፍትሔዎችን ከመስጠት ባለፈ የደንበኞቹን ዘለቄታዊ የአይቲ ፍላጎቶች እየፈታ ከደንበኞቹ ጋር አብሮ ያድጋል።

Related Post