አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል 2400 አምቡላንሶች ተሰራጩ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል 2400 አምቡላንሶች ተሰራጩ
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል 2400 አምቡላንሶች ተሰራጩ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከ2400 በላይ አምቡላንሶች ለክልሎችና ለከተማ መስተዳደሮች እንዲሁም በዚህ ስራ ለተሰማሩ ተቋማት ተሰራጭቷል፡፡

በአገራችን የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ ሪፖረት ከተደረገ ጀምሮ (መጋቢት 4 2012) የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ 19/ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችን አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግጫ እንደገለጹት ኮሮና ቫይረስን በአገር አቀፍ ደረጃ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በፌደራል፣ በየክልሎችና በየተቋማቱ ያሉትን አደረጃጀቶችና ተቋማት ዓቅም ለማጠናከርና ለመደገፍ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ መንግስት የችግሩን ጥልቀት አስቀድሞ በመገንዘብ የተለያዩ አደረጃጀቶችን ሚኒስቴር መስርያ ቤቶችን ጭምር በማደራጀት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በሙሉ ዓቅሙ እየሰራ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ 19/ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችን አስመልክቶ የተሠጠውን ሙሉ ማብራሪያ ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ማግኘት ይቻላል፡፡

Related Post