አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 7,673 ኤሌክትሪክ በ6 ወር አመነጨ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 7,673 ኤሌክትሪክ በ6 ወር አመነጨ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 7,673 ኤሌክትሪክ በ6 ወር አመነጨ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በግማሽ ዓመቱ በ9,080.7 ጌጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማምረት አቅዶ 7,673.4 ጌጋ ዋት በማምረት የዕቅዱን 84.5 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡

በግማሽ ዓመቱ ከሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ብር 4.4 ቢሊዮን ለማግኘት አቅዶ ብር 7.4 ቢሊዮን በማግኘት የዕቅዱን 168 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡ በውጭ ሀገር የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ረገድ 42.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት አቅዶ 46.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም የዕቅዱን 110 በመቶ ያገኘ ሲሆን፣ አፈፃፀሙ ከ2013 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ4.10 ሚሊዮን ዶላር ወይም በ10 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡



የኤሌክትሪክ ማስተላለፊ መስመሮችን ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ ባቀደው መሰረት የዕቅዱን 99 ማከናወን ችሏል፡፡ በግማሽ ዓመቱ ለ1,811 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ የነበረ ሲሆን ፣ በአፈጻጸሙ 1,746 ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናችሀዉን ከኢትዮጵያ የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደግሞ በግማሽ ዓመቱ  ከኤሌክትሪክ ሃይል (ከኢነርጂ) ሽያጭ ብር 10.85 ቢሊዮን ለማግኘት አቅዶ ብር 8.96 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 83 በመቶ አከናውኗል፡፡ ሌሎች ገቢዎችን ጨምሮ አጠቃላይ የመንፈቅ ዓመቱ ገቢው 11.15 ቢሊዮን ሆኗል፡፡

ብር 811 ሚሊዮን ትርፍ ከታክስ በፊት ማግኘት ችሏል፡፡ በዚህም ተቋሙ ከትርፋማነት አንጻር አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን ማየት ተችሏል፡፡ በዋና ዋና የፋይናንስ ጤናማነት መለኪያዎችም ሲታይ ድርጅቱ በመልካም የፋይናንስ አቋም ላይ እንደሚገኝ ተገምግሟል፡፡ በጦርነት ምክንያት ኃይል የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ስራ መከናወን መቻሉም በጠንካራ ጎን ተገምግሟል፡፡

አገልግሎቱ በአጋማሽ ዓመቱ 176 ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ማድረግ በመቻሉ በ2013 ዓ.ም. የነበሩትን ደንበኞች ቁጥር በ5.5 በመቶ አሳድጓል፡፡ የኃይል ተደራሽነትን ደግሞ በ2013 መጨረሻ ከነበረበት 44 በመቶ ወደ 47 በመቶ ማሳደግ የቻለ ሲሆን፣ የትራንስፎርመር ብልሽትን በታቀደው ደረጃ የመቀነስ ሥራ ተከናውኗል። በዕቅድ ተይዞ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግርን የመቅረፍም ተግባር ተከናውኗል፡፡



የዕለቱን ግምገማ የመሩት ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት በመንግሥት ደረጃ ትኩረት የሚሰጣቸው ተቋማት እንደሆኑ ገልጸው፣ በመንፈቅ ዓመቱ የድርጅቶቹን የፋይናንስ ቁመና ለማስተካከል የተከናወነ ተግባር እና በኤክስፖርት ጥሩ ውጤት እንደተመዘገበ ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ትርፋማ መሆን መጀመሩ አበረታች እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ከኤሌክትሪክ መቆራረጥ፣በወቅቱ የአገልግሎት ሂሳብ ከመሰብሰብ፣ ሂሳብ በጊዜ ዘግቶ ከማስመርመር፣የውጭ ምንዛሪ ከማግኘት እንዲሁም ከፕሮጀክት አፈጻጸም አንጻር ትኩረት ሰጥቶ መሠራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

 

Related Post