የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ከዪኒዶ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው እና በግብርና ማቀነባበሪያ ኢንቨስትመንት ሴክተር ዕድል እና አማራጮች ላይ ያተኮረ የኢንቨስትመንት ፎረም በዱባይ ተከሂዷል፡፡
ከተሳታፊ ባለሀብቶች ለተነሱ ጥያቄዎችም በምክትል ኮምሽነር ተመስገን ጥላሁን እና በኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ሳንዶካን ደበበ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡በመቀጠልም የኢንቨስትመንት ኮምሽን እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ልዑካን ቡድን የዲፒ ጀብልን የንግድ ዞን እና የተለያዩ የዱባይ ኢንቨስትመንቶችን ጎብኝተዋል፡፡
በቆይታቸውም የተለያዩ ባለሀብቶች እና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በፋርማሱቲካል፣በኮንስትራክሽን እና ሪል ስቴት፣ በግል ኢንቨስትመንቶች እና በኢንደስትሪ ፓርክ ልማት ሴክተር ለመሰማራት ፍላጎትን አሳይተዋል፡፡