አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ20% ቅናሽ አደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ20% ቅናሽ አደረገ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ20% ቅናሽ አደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ የትኬት ዋጋ ላይ ባደረገው የ20% ቅናሽ ተጠቃሚዎች የትኬት መቁረጫ እና የጉዞ ሰሌዳ ይፋ አደረገ።

የታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ ሁለተኛ ክፍል የሆነው ‘ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት’ ጥሪን ተቀብላችሁ ወደ ኢትዮጵያ ለምትመጡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ጉዞ ትኬት ዋጋ ላይ 20% ቅናሽ ማድረጉን አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ትኬታችሁን ከኤፕሪል 6 እስከ ኤፕሪል 21፣ 2022 በመቁረጥና ጉዟችሁን ከኤፕሪል 25 እስከ ሜይ 15፣ 2022 ድረስ በማመቻቸት የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንዲሁም ‘ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት’ ጥሪን ተከትሎ በተዘጋጁ ልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች ላይ እንድትታደሙ እንጋብዛለን።

Related Post