አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 27 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሰረዘ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 27 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሰረዘ
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 27 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሰረዘ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በቀድሞ ህግ ሰርተፍኬት የነበራቸው እና በቀድሞው ህግ ምዝገባ ጀምረው ለነበሩ 106 ፓርቲዎች በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ በደብዳቤ ማሳወቁን ገልጿል፡፡

ከቦርዱ ደብዳቤ ከደረሳቸው 106 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 76 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰነዶችን ያቀረቡ ሲሆን በሕጉ መሠረት ተሟልቶ የቀረበ ስለመሆኑ እየተመረመረ ይገኛል ብሏል ቦርዱ፡፡
ምርመራ የሚደረገውም ይላል ቦርዱ፤
• ፓርቲዎቹ በደብዳቤ የተገለጸላቸውን ነጥቦች ሁሉንም ማሟላታቸውን ማረጋገጥ (የህገደንብ ለውጥ ጠቅላላ ጉባኤ ሰነዶች አቀራረብ፣ የመስራቶች ፊርማና የመሳሰሉት)
• የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕጉ መሠረት ማሟላት የሚገባቸውን የመሥራች አባላት ብዛት ትክክለኛነትን ለመፈተሽ ካቀረቡት የመሥራች አባላት ዝርዝር ናሙና የማውጣት
• ናሙናዎቹ በትክክል ግለሰቦቹ የተፈረሙ መሆናቸውን ወደተፈረሙበት ቦታ በመላክ ማረጋገጥ
• የህገ ደንብ ለውጦችና፣ የጠቅላላ ጉባኤ ሰነዶች በትክክል መያያዛቸውን ማረጋገጥን ያጠቃልላል፡፡
ይህ እንደተጠናቀቀም ሰነዶቻቸው ካስገቡት 76 ፓርቲዎች መካከል ምን ያህሎቹ መስፈርት እንዳሟሉ በቦርዱ ይፋ የሚደረግ ይሆናል፡፡
ነገር ግን የሚጠበቅባቸውን ሰነድ ማስገባት ያልቻሉ እና ጊዜ እንዲራዘምላቸው የጠየቁ 16 የፓለቲካ ፓርቲዎች ሲኖሩ ከነዚህ ፓርቲዎች መካከል ከስር የተጠቀሱት የ13ቱ አጥጋቢ ምክንያት ባለማቅረባቸው እንዲሰረዙ ቦርዱ ወስኗል፡፡
የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ሳያገኝ የተዘረዙ ፓርቲዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው
1. የኢትዮጵያውን ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ (ኢዴአን) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ
2. የገዳ ስርአት አራማጅ ፓርቲ (ገሥአፓ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
3. የየም ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( የብዴን) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ
4. የደንጣ ዱባሞ ክችንችላ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት – የመስራች አባላት ዝርዝርም ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ
5. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ ( ኮንግረስ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
6. የትግሪ ወርጂ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ( ትወብዴድ) – ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ
7. የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ፣ ጉባኤም ያላካሄደ
8. የኢትዮጵያን አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢአዴድ) – ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ
9. የመላው አማራ ህዝብ ፓርቲ (መዐሕፓ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
10. የኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
11. የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኮንግረስ ( ደቡብ ኮንግረስ) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
12. የሸኮና አካባቢው ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሸአሕዲድ) -ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ
13. ነጻነትና ሰላም ለኢትዮጵያ ህብረት ፓርቲ ( ነጻነትና ሰላም) – የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ
በሌላ በኩል ሌሎች 14 ፓርቲዎች ደግሞ ከቦርዱ በተደረገው ጥሪ መሰረት ሰነዶቻቸውን ከነጭራሹያላቀረቡ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መዋሃዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የነዚህ 14 ፓርቲዎች እንዲሰረዙ ቦርዱ ወስኗል፡፡
በመሆኑም ሰነድ ባለማምጣታቸው እንዲሰረዙ የተሰወኑት ፓርቲዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ
2. መላው ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
3. የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ
4. የሐድያ ብሔር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
5. የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት
6. የዲል ወቢ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
7. የቤንች ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
8. የስልጤ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
9. የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ
10. የሱማሌ አንድነት ፓርቲ
11. ነፃነት ለአንድነትና ለፍትሕ ፓርቲ
12. ብሔራዊ ተሀድሶ ለሰላም ልማት
13. የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት
14. የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ
ሁለት ፓርቲዎች ሰነዶችን ማቅረብ አለመቻላቸው በፓርቲው የውስጥ ችግር የተነሳ መሆኑ ስለታመነበት ጠቅላላ ጉባኤያቸውን የኮቪድ ወረርሽን በሚያበቃበት ወቅት አንዲያከናውኑ ቦርዱ ሲወስን ሌሎች ሰነዶቻቸው ግን ከላይ በተጠቀሰው መንገድ እየተገመገሙ ይገኛል፡፡
በልዩ ሁኔታ የሰነድ ካስገቡ ፓርቲዎች ጋር ሰነዶች እንዲታይላቸው የተደረጉ ፓርቲዎች
1. ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ( ኢዴፓ)
2. ወለኔ ህዝቦች ፓርቲ

Related Post