አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የኢትስዊች አመታዊ ትርፍ በ153 በመቶ አደገ

ኢትስዊች እ.ኤ.አ 2021/22 በጀት ዓመት የተጣራ ትርፍ ከታክስ በፊት በ153 በመቶ በማደግ ወደ ብር 221 ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ።

እ.ኤ.አ 2021/22 በጀት አመት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ስዊች የሆነው ኢትስዊች አ.ማ በአሰራር እንቅስቃሴ፣ በገቢ ማስገኛ እና በፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ የላቀ ውጤት አስመዝግቧል። ኢትስዊች የመጀመሪያውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂ በጁላይ በእ.ኤ.አ 2020 መተግበር የጀመረ ሲሆን የኢትስዊች ዳይሬክተሮች ቦርድ ባሳለፍነው ዓመት ድርጅቱን ለማሳደግ የሚረዱ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎች፣ በድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ የተደረጉ ለውጦችን መርምሮ አጽድቋል። ይህም አወቃቀሩ፣ የሰው ሀብት ፖሊሲ፣ የሂሳብ ፖሊሲ፣ የግዥ ፖሊሲ፣ የደመወዝ ስኬል እና የጥቅማ ጥቅሞች ጥቅል ማሻሻልን ይጨምራል።

ይህም ጥንቃቄ የተሞላበት የወጪ አስተዳደር ውጤት እና በጠቅላላ ገቢ እድገት ውጤት ነው። በበጀት ዓመቱ ኢትስዊች 329.8 ሚሊዮን ብር ገቢ ያስገኘ ሲሆን ከዕቅዱ 110 በመቶውን በማሳካት ካለፈው ዓመት ደግሞ የ84 በመቶ እድገት አስመዝግቧል።

እ.ኤ.አ.2021/22 የበጀት አመት የባንክ ኢንዳስትሪው በአጠቃላይ 171,068,129 የኤቲኤም ግብይቶች ያከናወነ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 39,894,113 የሚሆኑት በኢትስዊች በኩል የተስተናገዱ ናቸው። እነዚህ ግብይቶች ከ 44 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆኑ ናቸው።

በተመሳስይ በኢንዱስትሪው 62,183,090,000 ብር የሚሆኑ በድምሩ 2,339,255 የፖስ ግብይቶች የተደረጉ ሲሆን ከኒዝህ ውስጥ 361,321 እነዚህ ግብይቶች 856,970,160 ብር ይገመታሉ። (ከባለፈው ዓመት የ230 በመቶ ጭማሪ ያለው) የሚሆኑት በኢቲስዊች የተሳለጡ ናቸው። ሁሉም አባል ባንኮች አሁን በፖስ ተናባቢነት (interoperability) አገልግሎት ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በበጀት ዓመቱ ኢትስዊች 301,293 የሚሆኑ የካርድ እና የፒን ፐርሰናላይዜሽን (personalization) አገልግሎት የሰጠ ሲሆን ካለፈው አመት አንጻር የ7 በመቶ እድገት አሳይቷል። በብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የተሰጣቸው አዳዲስ ባንኮች ኢትስዊችን እንደ አባል በመቀላቀላቸው ይህ አገልግሎት በፍጥነት እንደሚስፋፋ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ዓመቱ ከሙከራ ሙሉ አገልግሎት ወደ መስጠት ደረጃ ባደገው ከባንክ ወደ ባንክ ገንዘብ የማስተላለፍ (P2P transfer) አገልግሎት 2,063,534 ግብይቶች በድምሩ ብር 19,999,726,018 ተመዝግቧል። ይህ በፍጥነት እያደገ ያለ እና ትልቅ አቅም ያለውአገልግሎት ነው።

ከኢንተርናሽናል ካርዶችን በተመለከተ፣ ኢትስዊች በአሁኑ ጊዜ ማስተር ካርድ፣ ቪዛ እና ዩኒየን ፔይ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ ከበርካታ የክፍያ ጥምረቶች ጋር በመስራት ላይ ይገኛል።

ባንኮች እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት በአለም አቀፍ ደረጃ የተገናኘውን ኔትዎርክ መጠቀም ከፈለጉ ኢትስዊችን እንደ የሶስተኛ ወገን የክፍያ ፕሮሰሰር ሊጠቀሙ ይችላሉ። የኢትዊችን ሲስተመ ከማስተር ካርድ ጋር ለማያያዝ የተጀመረው ፕሮጀክት በበጀት አመቱ 100% ተጠናቅቋል በሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛል። EthSwitch የዲስከቨር ካርድ አባልነት ስራንም በማካድሄ ላይ ይገኛል።

ኩባንያችን ክፍያን ለማዘመን፣ በፋይናንሻል ተቋማት መካከል እርስ በራስ ተነባቢነትን /interoperability/ ለማጎልበት እንዲሁም የጋራ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት የሚረዱ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህነም መሰረት የሚከተሉት አንኳር ፕሮጀክቶች ቀርጾ በመተግር ላይ ይገኛል፡፡
1. Instant Payment Switch
2. ዓለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የክፍያ ጌትዌይ (Payment Gateway)
3. እንደባንኮች ፍላጎት የሚያገለግሉ የጋራ የሞባይል ዋሌት እና መሰል ሴስተሞች (White-Label Shared Wallet)
4. የጋራ ሪኮንስሌሽን ሲስተም (Shared Reconciliation system)
5. የጋራ የደህንነት ማዕከል (Shared Security Operation Center) ማቋቋም

በያዝነው በጀት ዓመትም ኢትስዊች አ.ማ. የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአይነትም ሆነ በአገልግሎት ጥራት የተሻሉ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ እንዲሁም በአምስት ዓመት ስትራቴጂው መሰረት በሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን መጨረስ፣ የማስፋፊያ ምዕራፍ ላይ ያሉ ውጥኖችን ማጠናቀቅ፣ ስትራቴጂውን መገምገም፤ ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎችን ለማስጀመር የሚያስችሉ ትስስሮችን መፍጠር እና ኩባንያችንን ለሶስተኛው የ‘Blue Sky’ የስትራቴጂ ምዕራፍ ማዘጋጀት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል፡፡

ስለ ኢቲስዊች፦ እ.ኤ.አ. በ2011 የተቋቋመው ኢትስዊች የአክሲዮን ማህበር በሁሉም ባንኮች እና በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ በርካታ ማይክሮፋይናንስ ድርጅቶች ባለቤትነት የተያዘ ነው። በዋናነት ቀላል፣ ተመጣጣኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የኢ-ክፍያ መሠረተ ልማት አገልግሎቶችን ለችርቻሮ ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ለማቅረብ የተቋቋመ ውነ።

ከከፍተኛ ክህሎትና ከባለሙያዎች በመደገፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ ላይ የሚገኘው ኢትስዊች በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የብሔራዊ ክፍያዎችን ማዘመንና እና ለፋይናንስ አካታችነት አስተዋፅኦ እያደረገ ነው። ከ2016 ጀምሮ በሁሉም ባንኮች የሚሰሩ የኤቲኤም እና የPOS መሳሪይዎች ተናባቢነት እንዲኖር አስችሏል። በአሁኑ ጊዚ ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት የሚደረግን የገንዘብ ዝውውርን ተናባቢ የማድረግ አገልግሎትን ዘርግቷል።

Related Post