አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትርጉምና አስተርጓሚነት ትምህርት ሊሰጥ ነው

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትርጉምና አስተርጓሚነት ትምህርት ሊሰጥ ነው

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትርጉምና አስተርጓሚነት ትምህርት በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሂዩማኒቲ ስኩል የማህበራዊ ሥነ ልሳን መምህር የሆኑት ዶክተር መስፍን ወዳጄ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ትምህርቱን ለመስጠት እንዲያስችል ሥርዓተ ትምህርት( ካሪኩለም) በማዘጋጀትና የዘርፉን ምሁራን እንዲሁም የሚመለከታቸውን አካላትንም በመጠየቅ የዳሰሳ ጥናት ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያ የቋንቋ ብዝኃነት ያለባት ሀገር እንደመሆኗ መጠን የትርጉም ትምህርት አለመሠጠትም አስገራሚ የሚባል እንደሆነም ዶክተር መስፍን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በሀገራችን በመጀመሪያ ዲግሪም ይሁን በሁለተኛ ዲግሪ በሥነ ትርጉም ክፍል የሚያስመርቅ አልነበረም፤ ይሁን እንጂ ትምህርቱን መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ከጥናቱ ላይ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ሰዓት ከ400 ሚሊዮን ብር በመበጀት የተለያዩ የማህበሰብ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት በተለያዩ ክ/ከተሞች የሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ሰርቶ ለነዋሪዎቹ አበርክቷል፡፡

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ይህ ምግባር በሁሉም ትምህርት ተቋማት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ሀገር የምታድገው በመረዳዳትና በመተጋገዝ ጭምር ሲሆን እነኚህን ሰዎች ለሀገራቸው በጊዜአቸው ባለውለታዎች እንደነበሩ አክለው ተናግረዋል፡፡

(ምንጭ – ኢ ፕ ድ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ )

Related Post