አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የአዘርባጃን ሕዝብ የጃንዋሪ ጥቁር ቀን አክብረዋል

የአዘርባጃን ሕዝብ የጃንዋሪ ጥቁር ቀን አክብረዋል
የአዘርባጃን ሕዝብ የጃንዋሪ ጥቁር ቀን አክብረዋል

የአዘርባጃን ሕዝብ የጃንዋሪ ጥቁር ቀን አክብረዋል፡፡ 30ኛ ክብረ-በዓል፣ ጥር 12 ቀን፣ የጃንዋሪ ጥቁር ቀን፣ ባኩ 1990፣ የሶቭየት ወረራ፣ የቀዩ ሠራዊት ሽብር፡፡ በጃንዋሪው ደም መፋሰስ ክስተት ተጠቂዎች በሕሊና ጸሎት ተከብሯል፡፡

በጥር 11-12 ቀን 1982 ዓ.ም ምሽት የሶቭየት ወታደሮች የአካባቢውን ሕዝብ ሳያሳውቁ ሳይታሰብ ባኩን አጥቅተው በሁሉም በኩል ጥቃት ፈጽመው ባህሩንም ጨምሮ ጥቃት አድርሰው የአዘርባጃንን ሕዝብ የነጻነት አንቅስቃሴ እንዲወድቅ ጥቃት ፈጽመዋል፡፡

ወታደሮቹ ሳይለዩ ሴቶች፣ በዕድሜ የገፉ እና ሕጻናት ላይ ተኩስ ከፍተው የአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ ጨምሮ እና ዶክተሮች ላይ ተኩስ በመክፈት ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ፈጽመዋል፡፡ ታንኮች እና ብረት ለበሰ ተሽከርካሪዎች ሲቪሎችን በመግጨት፣ በመሰባበር ሰዎች ያሉበትን የሕክምና ተሽከርካሪ ላይ ጨምሮ ጥቃት አድርሰዋል፡፡

በዚህም ከባድ ጥቃት 147 ሲቪል ሰዎች ለሞት እና 800 ያህል ሰዎች ለጉዳት ዳርጓል፡፡ ያለው እውነታ በሶቭየት ቤቶች የደረሰው ጥቃት በጣም የተለየ ነበር፤ አያይዞም በዲ. ያዞፍ የዩኤስኤስአር መከላከያ ሚኒስቴር እንደተገለጸው ባኩ ላይ ሃይል መጠቀም ኮሙኒስት ባልሆኑ ተቃዋሚዎች አዘርባጃ ውስጥ ስልጣን መያዝ ለመከልከል እና ኮሙኒስት መንግስት በስልጣን ላይ እንዲቆይ ለማድረግ ነው የታሰበው ብለዋል፡፡

ይህ ብጥብጥ የተሞላበት ጥቃት አዘርባጃን ውስጥ ለ70 ዓመታት የነበረውን የሶቭየት አገዛዝ እንዲያበቃ እና ብሔራዊ ነጻነት እንዲመሰረት አድርጓል፡፡

ሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት አዘርባጃን የጃንዋሪው ጥቁር ቀን ላይ በእርግጥ በሶቭየት ወታደር ሃይል በጥር 11-12 ቀን 1982 ዓ.ም የተፈጸመው ግድያ የአዘርባጃን ሕዝብ ያለውን አቋም እንዲያወጣ እና ለነጻነት መከበር እንዲታገል አድርጎታል፡፡

Related Post