አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሊቀበል ነዉ

የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሊቀበል ነዉ
የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሊቀበል ነዉ

ባለፈዉ 2012 የትምህርት ዘመን መጋቢት ወር ላይ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆዉን የመማር ማስተማር ስራ ለማስጀመር በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈዉ አቅጣጫ መሰረት በቅድሚያ ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ የሚያስችሉ ዝግጅቶችን መጠናቀቃቸዉን ተገለፀ፡፡

ይህ የተገለፀዉ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዶክተር መልካሙ ደሬሳ ነዉ፡፡ ባለፉት ወራት ዩኒቨርሲቲዉ በክልሉ በወረርሽኙ ለተጠረጠሩ ለይቶ ማቆያነት ሲያገለግል ለ1 ሺህ 4 መቶ ተጠርጣሪዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን ሲሰጥ ቢቆይም በአሁኑ ሰዓት ሁሉም የአገልግሎት መስጫ ህንፃዎች ተፀድተዉና ታድሰዉ ለመማር ማስተማር ስራዉ ዝግጁ መሆናቸውንም ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲዉ የተማሪዎች መሰረታዊ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ወንድም መኩሪያዉ በሚኒስቴሩ በተላለፈዉ አቅጣጫ መሰረት የተማሪዎች መኝታ፣ የመመገቢያና ተያያዥ አገልግሎት የሚሰጥባቸዉ ቦታዎች አካላዊ ርቀትን ለማስጠበቅ ሲባል ቀደም ሲል ከሚይዙት ቁጥር በግማሽ ቀንሰዉ እንዲስተናግዱ ዝግጅት መደረጉንና ለጽዳትና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚዉሉ ዉሃና ሌሎችም የንፅህናና ደህንነት መጠበቂያ ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ መዘጋጀታቸዉን ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ሲገቡ በጤና ሚኒስቴርና በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጡ የጥንቃቄ ደንቦችና መስፈርቶችን በአግባቡ እንዲተገብሩና ክፍተቶች ሲኖሩም በልዩ ሁኔታ ለመከታተልና ለመቆጣጠር ከህግ አገልግሎትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አዲስ የዲሲፕሊን መመሪያና ደንብ ተዘጋጅቷል ያሉት ዳይሬክተሩ ለዚህም በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ የቅድመ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከአጠቃላይ የእድሳትና የፅዳት ስራዎች ባሻገር ቀድመዉ ለሚገቡ 1 ሺህ 7 መቶ 26 ተመራቂ ተማሪዎች በተቀመተዉ መስፈርት መሰረት የመኝታ፣ የምግብና ሌሎችም መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት በቂ ዝግጅት መጠናቀቁን የገለፁት የተማሪዎች መሰረታዊ አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ሁሉም እንቅስቃሴ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚያስችል ሁኔታ ታሳቢ መደረጉንም አብራርተዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና የፌደራል ባለድርሻ ተቋማት ቡድን የተቋሙን ቅድመ ዝግጅት ተመልክቶ በሚሰጠዉ አቅጣጫ የተማሪዎች ቅበላ እንደሚካሄድም ከዩኒቨርሲቲዉ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለክልሉ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቁት

Related Post