አርእስተ ዜና
Sun. Jan 26th, 2025

የአርብቶ አደሮች ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ

የአርብቶ አደሮች ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ
የአርብቶ አደሮች ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ

በየኔነህ ሲሳይ – በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ትላንት የተከፈተው የምስራቅ አፍሪካ የአርብቶ አደሮች ኤክስፖ ለቀጣዮቹ ቀናት ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል።

በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የድንበር አካባቢዎች የሚኖሩ እፕርብቶ አደሮች ተመሳሳይ የአኗኗር ባህል እና የስነ ልቦና አንድነት ስላላቸው ሀገራቱ በጋራ መስራት ከቻሉ ግጭቶች እንዳይኖሩ ማድረግ ይቻላል ተብሏል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት / ኢጋድ / የአርብቶ አደር እና የእንስሳት ሀብት ማዕከል ICPALD ዳይሬክተር ደረጀ ዋቅጅራ (ዶ/ር) የኤክስፖውን መከፈት ምክንያት በማድረግ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጠት ማብራሪያቸው የምስራቅ አፍሪካ የአርብቶ አደሮች ሚና ከሀገራቱ ልማት እና እድገት በተጨማሪ ግጭቶችን የመከላከል ድርሻቸው ከፍተኛ በመሆኑ መንግስታት በጋራ ከመስራት በላይ ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ድጋፎችን መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

አርብቶ አደርነት አንዱ የኑሮ ዘየ በመሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ፣ በተለይም በድርቅ ወቅት እና ዝናብ በሚጠፋበት ጊዜ አርብቶ አደሩ በቀላሉ የእንስሳት ሀብቱን እንዳያጣ ለክፉ ቀን የሚሆንን የእንስሳት መኖ አያያዝ እና ክምችት ላይ ሀገራት ሊሰሩ ይገባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል ።

ICPALD የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮችን አቅም ለማሳደግ እና የእንስሳት ሀብቶቻቸው ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ላለፉት አስር አመታት እየሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ዶክተር ደረጄ በዚህም ብዙ ለውጦች መምጣታቸውን ገልፀው መንግስታት ለአርብቶ አደሩ የተሻለ ስራዎችን እንዲሰሩ መንገድ አሳይቷል ብለዋል። በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሚሊኒየም አዳራሽ ትላንት ጃንዋሪ 26 የተከፈተው የምስራቅ አፍሪካ የአርብቶ አደሮች ኤክስፖ እስከ ፌብርዋሪ 1, 2024 በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚቀጥል እና ለፓሊሲ አውጭዎች ግብአት ይሆናሉ የተባሉ ሰባት የጥናት ወረቀቶችም እንደሚቀርቡበት ሰምተናል።

Related Post