አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ተካሄደ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ተካሄደ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ተካሄደ

ዛሬ ለኢትዮጵያ የብርሀን መባቻ ነውና መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ የአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ የህዳሴ ግድብ ሥራ መጀመሩን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት÷ ይህ ለአኅጉራችን እንዲሁም አብረናቸው ሠርተን በጋራ ለመጠቀም ለምንሻ የታችኛው ተፋሰስ አገራት የምሥራች ነው ብለዋል። “ዛሬ የአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ የህዳሴ ግድብ ሥራውን ጀምሯል። ይህ ለአኅጉራችን እንዲሁም አብረናቸው ሠርተን በጋራ ለመጠቀም ለምንሻ የታችኛው ተፋሰስ አገራት የምሥራች ነው።” ሲሉ የብስራት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡



ጠቅላይ ሚር ዐቢይ አሕመድ ለህዳሴው ግድብ ከጥንስሱ እስከ ስኬቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሀገር መሪዎች እና ለተለያዩ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለግድቡ እዚህ ደረጃ መድረስ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በዚህም
1. ቀዳማዊ ሃይለስላሴ
2. የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ
3. የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ
4. የቀድሞ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ
5. የቀድሞ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ
6. ዶክተር ምህረት ደበበ
7. ኢንጂነር አዜብ አስናቀ
8. ኢንጂነር ስመኘው በቀለ
9. ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ
10. ዲክተር አብርሃም በላይ
11. አቶ ግርማ ብሩ
12. የህዳሴ ግድብ ሰራተኞች
13. የሃገር መከላከያ ሰራዊት
14. የዳያስፖራ አባላት
15. የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት
16. የኢትዮጰያ ህዝብ ለግድቡ እውን መሆን ለነበራቸው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

በዚህም መሰረት አጼ ኃይለሥላሴ በዚያን ጊዜ ፕሮጀክቱን መፈጸም ባይችሉ እንኳን ቀጣዩ ትውልድ ይገነባዋል ብለው በማመን የፕጀክቱን ሀሳብ እና ዲዛይን በመቅረጻቸው እጅግ ምስጋና ይጋባቸዋል ነው ያሉት፡፡



“አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፕሮጀክት በጅምር በቁፍሮ ከነበረበት ጊዜ ላይ ተረክበው እስከደረሰበት ደረጃ ለማድረስ በእሳቸው ጊዜ ያልነበረው ምቹ ሁኔታ ና አውድ ሳያግዳቸው ላደረጉት ተጋድሎ ምስጋና ይገባቸዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ እድለኛ ሆነው ዛሬ ከእኛ ጋር ይሄንን ድል ለማየት ስለበቁ በከፍተኛ አድናቆት እንኳን ደስ ያለዎት ልላቸው እፈልጋለሁ።” ብለዋል፡፡

ከንጉሡ በኋላም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ጊዜው አሁን ነው ብለው ፕሮጀክቱን በማስጀመራቸው ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም ደሣለኝም ፕሮጀክቱን በማስቀጠል የራሳቸውን ገንቢ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ሶስቱም አመራሮች የጀመሩት ፕሮጀክት ስለሆነ እኛ ለውጤት ያበቃነው ማመስገን ግድ ይለናል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦርድ አመራርሮችን፣ ባለሙያዎች፣ የህዳሴ ግድብ ሰራተኞች፣ የመከላከያና የፀጥታ ሃይሎችን እንዲሁም መላው ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አመደግናለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

Related Post