አርእስተ ዜና
Tue. Nov 12th, 2024

የብሔራዊ ህጋዊ ስነ-ልክ ረቂቅ አዋጅ ለዉይይት ቀረበ

የብሔራዊ ህጋዊ ስነ-ልክ ረቂቅ አዋጅ ለዉይይት ቀረበ
የብሔራዊ ህጋዊ ስነ-ልክ ረቂቅ አዋጅ ለዉይይት ቀረበ

የብሔራዊ ህጋዊ ስነ-ልክ ረቂቅ አዋጅ እና የኢትዮጽያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ረቂቅ አዋጆች ለኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱ የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አይሻ ያህያ የአዋጆች መዘጋጀት የአሰራር ስርዓቶችን ለማሻሻልና የዘርፋን ውጤታማነት ለማሳደግ እንደሚያስችል ገልፀዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት መሰረተ ልማት ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን በበኩላቸው ጠንካራና ውጤታማ ተቋማትን መፍጠር ጠንካራ ሀገርን ለመገንባት እንደሚያስችል ገልፀው የረቂቅ አዋጆቹ መዘጋጀት የዘርፋን ውጤታማነትን በማሻሻል በአለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችለል ሲሉ አብራርተዋል።

በረቂቅ አዋጆቹ ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን በየደረጃው በሚገኙ ባለድርሻ አካላት፣ ባለሙያዎችና አመራሮች ግብአቶች ከተለያዩ ሀገሮች በተገኙ ልምዶች እንዲዳብር ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑም በመድረኩ ተገልጿል።

Related Post