አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ተመረቀ

የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ተመረቀ
የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ተመረቀ

300 አውቶብሶችን ማቆም የሚችለውና ዘመናዊ የጥገናና የተለያዩ አገልግሎቶችን ያካተተው የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ተመረቀ።

የአውቶብስ ዴፖውን መርቀው ስራ ያስጀመሩት ኢ/ር ታከለ ኡማ ናቸው። ዴፖው ከመሬት በታች የሚገኝ የአውቶብስ ማቆሚያን ያካተተ ነው። የቃሊቲ አውቶብስ ዴፖ ዘመናዊ ጋራዥ፣ዘመናዊ ነዳጅ ማደያዎችን፣የአውቶቡሶችን ውጭ አካል ቀለም መቀባት የሚችል እንዲሁም አንድን አውቶብስ ከሁለት ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ማጠብ የሚችል መሳሪያ ተገጥሞለታል።

የዴፖው መጠናቀቅ በከተማዋ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በስኬት መጠናቀቅ የጀመርነውን መጨረስ እንደሚቻል ማሳያ ናቸው ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ በከተማዋ የተያዙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ የሚጠናቀቁ አዳዲስ ፕሮጀክቶችም የሚጀመሩ ይሆናል ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋ ትራንስፖርት ስርአትን ማዘመን ላይ ትኩረት አድርጓል ያሉት ኢ/ር ታከለ በተለይም በመካከከለኛና በዝቅተኛ የኑሮ እርከን ላይ የሚገኙ ዜጎችን የሚገለገሉባቸው የትራንስፖር አማራጮችን ማሳደግና ማዘመን የከተማ አስተዳደሩ ዋነኛ ትኩረት ናቸው ብለዋል።

በዛሬው እለት የተመረቀው የቃሊቲ አውቶብስ ዴፖ ከአውቶብስ እጥበት የሚወጣው 80 በመቶ ፍሳሽ የሚያጣራና በድጋሚ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያደርግ (water recycling treatment plant) እንዲሁም ከዲፖው የሚወጣውን ቆሻሻ ፍሳሽ አጣርቶ ዝቃጩን የሚያስቀር ቴክኖሎጂ (waste water treatment plant) እንደተገጠመለት የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። አዲስ የተመረቀው የቃሊቲ አውቶብስ ዴፖ ከወራት በፊት ከተመረቀው የሸጎሌ አውቶብስ ዴፖ ቀጥሎ ሁለተኛው ነው። በመርካቶ አካባቢ ተጨማሪ የአውቶብስ ዴፖ በግንባታ ላይ ይገኛል።

Related Post