አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

የቀድሞዉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዳራሽ ወደ ሙዚየም ሊቀየር ነው

የቀድሞዉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዳራሽ ወደ ሙዚየም ሊቀየር ነው
የቀድሞዉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዳራሽ ወደ ሙዚየም ሊቀየር ነው

አዲስ አበባ የሚገኘዉን የቀድሞዉን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዳራሽ ወደ ታሪካዊ ሙዚየምነት ለመቀየር የማስዋብ ስራ ዛሬ ተጀመረ።

የማስዋቢያ ወጭው 57 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን የሚሽፈነው በተባበሩት መንግስታት እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል። የማስዋብ ስራው ሁለት አመት እንደሚፈጅ የተነገረ ሲሆን የኢትዮዽያ መንግስት ለመኪና ማቆሚያ የሚሆን ተጨማሪ ቦታ በነጻ ማበርከቱ ተነግሯል።

ካሳንችስ አካባቢ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚስሽን ቅጥር ጊቢ ዉስጥ የሚገኘው የድሮ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዳራሽ በአጼ ሃይለስላሴ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1961 እንደተመረቀ ይታወቃል። የድሮ የአፍሪካ አንድነት አዳራሽ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲመሰረት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1963 የአፍሪካ መሪዎች የታደሙበት መሆኑ ይታወሳል።

ይህንን ታሪካዊ ኩነት ለመዘከር አዳራሹን ወደ አፍሪካ ሙዚየምነት እንዲቀየር የተወሰነው ከአመታት በፊት መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። ከሁለት አመት በኋላ እድሳቱ ሲያልቅ አፍሪካን የሚገልጹ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽኖች እንደሚያካትት ለመረዳት ተችሏል።

የቀድሞዉን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዳራሽን ካስዋቡት መካከል በታዋቂው ኢትዮዽያዊ ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መስታወት መስኮቶች ላይ የተቀረጹ ድንቅ ምስሎች ይገኙበታል።

Related Post