አርእስተ ዜና
Tue. Dec 24th, 2024

የምስራቅ አፍሪካ የሚኒስትሮች የፍልሰት ጉዳዮች ፎረም እየተካሄደ ነው

የምስራቅ አፍሪካ የሚኒስትሮች የፍልሰት ጉዳዮች ፎረም እየተካሄደ ነው
የምስራቅ አፍሪካ የሚኒስትሮች የፍልሰት ጉዳዮች ፎረም እየተካሄደ ነው

አምስተኛው የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሚኒስትሮች ቀጣናዊ የፍልሰት ጉዳዮች ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የቀጣናው አባል ሀገራት፣ የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስትታት ድርጅት (ኢጋድ) እና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛል።

መድረኩ በቀጣናው አባል ሀገራት መካከል የሚስተዋለውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፍልሰተኞች ቁጥር ለመቆጣጠር በፖሊሲ የተደገፈ ምክረ ሃሳብ ለማስቀመጥ የሚያስችል መሆኑ ታውቋል።

በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሰፊ የፍልሰተኞች ቁጥር ያላቸውና መተላለፊያ የሆኑ ሀገራት፤ በዘርፉ የአስተዳደር ስልቶችን የተመለከተ የልምድ ልውውጥ በማድረግ በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ተገልጿል።

ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት በሚዘልቀው የምክክር መድረክ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሶማሊያ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳን፣ የኡጋንዳ፣ የሩዋንዳ፣ የታንዛኒያ፣ የብሩንዲ፣ የኤርትራና የጅቡቲ ተወካዮች እየተሳተፉ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Related Post