አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የህትመትና እና ፓኬጂንግ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ

የህትመትና እና ፓኬጂንግ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ
የህትመትና እና ፓኬጂንግ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ

የአፍሪ ፕሪንት እና ፓኬጂንግ የሳይን እና ግራፊክስ ኤክስፖ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ ፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ተስፋ ሰጪ የኢኮኖሚ አፈፃፀም አሳይታለች ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኢንዱስትሪ መሠረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ አማካሪ አቶ ዳንኤል ኦላኒ ሀገሪቱ በትምህርት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ለኢኮኖሚ ኢንደስትሪላይዜሽን መንገድ የሚከፍት የተሻለ ውጤት እያሳየች እንደምትገኝ በኤክስፖው ላይ ተገኝተው ገልፀዋል።

የአምራች ዘርፉን ምርታማነት ለመጨመር ካለፈው ዓመት ጀመሮ የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የተጀመረ ሲሆን ንቅናቄው በጥቂት ወራት ዉስጥ ለውጦች መምጣታቸውን ተናግረዋል። እንደ አቶ ዳንኤል ኦላኒ ገለፃ ከአምራች ዘርፉ ማደግ ጋር ተያይዞ የፓኬጂንግ ኢንዱስትሪው እየተስፋፋ የሚገኝ ሲሆን ከውጭ ሃገር ሲመጡ የነበሩ ምርቶች በሃገር ውስጥ መተካታቸው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም በውጭ ምርቶች ላይ የነበረንን ጥገኝነት በማስቀረት ተወዳዳሪነታችንን መጨመር የሚቻል አቅም ላይ እንድንገኝ አስችሎናል ብለዋል፡፡
የህትመት እና ፓኬጂንግ ስራዎች ከማንፋክቸሪንግ እድገት ጋር የሚነጣጠሉ አይደሉም ያሉት አቶ ዳንኤል በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚመረቱ ምርቶችን ለውጪ እና ሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ደረጃውን የተጠበቀ የህትምትና የፓኬጂንግ ስራዎች ወሳኝ ናቸው ብለው ከማኒፋክቸሪንግ እድገት ጎን ለጎን የህትመት እና ፓኬጂንግ ስራዎች ማደግ አለባቸው ብለዋል፡፡

መንግስት ለህትመትና ፓኬጂንግ ዘርፉ ተግዳሮት የሆነውን የፐልፕ እና ወረቀት ውድነት መፍትሄ ይሆናል ተብሎ የሚታመንበትን የፐልፕ ምርት በሃገር ውስጥ ለማምረት የአዋጭነት ጥናት እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

Related Post