አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

ዋን ዉሃ ምርቱን በዘጠይኝ እጥፍ አሳደገ

ዋን ዉሃ ምርቱን በዘጠይኝ እንጥፍ አሳደገ
ዋን ዉሃ ምርቱን በዘጠይኝ እንጥፍ አሳደገ

ዋና የተጣራ ዉሃ የማምረት አቅሙን ከ14,000 ሊትር በሰአት ወደ 120,000 ሊትር በሰአት ማሳደጉን ገለፀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እንየዉ ዘለቀ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ በተለይ እንደተነናገሩት እየጨመረ የመጣዉን የዋን ዉሃ ፍላጎት ለሟሟላት ድርጅቱ የማስፋፊያ ስራዎችን በመስራቱ የማምረት አቅሙን በዘጠኝ እጥፍ ገደማ አሳድጏል፡፡

ዋን ዉሃ የሚመረተዉ ሞግል የታሸገ ዉሃ አምራች በተባለዉ የአባሀዋ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እህት ኩባንያ መሆኑን የገለፁት አቶ እንየዉ በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ ከባለ 350 ሚሊ ሊትር እስከ ባለ ሃያ ሊትረ ጃር የታሸገ ዉሃ እያመረቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዋን ዉሃ ከ500 በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል እንደፈጠረም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ገልፀዋል፡፡የዛሬ ሁለት አመት በኢትዮጵያ 67 ገደማ የነበረ የታሸገ ዉሃ አምራች ኩባንያዎች በአሁኑ ወቅት ወደ 100 አካባቢ እንደሚጠጉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የታሸገ ዉሃን ለኢትዮጵያ ገበያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዛሬ ሁለት አሰርት አመታት በፊት ያስተዋወቀዉ ታዋቂዉ ኢትዮጵያዊ የቢዝነስ ሰዉ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ሲሆኑ የዉሃዉንም ስያሜ ‘ሀይላንድ’ እንደነበረ ይታወሳል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=P8nCIHmdE4k[/embedyt]

Related Post