አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

ዋልያ ሁለተኛ የብረታ ብረት ፋብሪካ ሊከፍት ነዉ

ዋልያ ብረታ ብረት ኢንደስትሪ ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ ከዉጭ ባለሀብቶች ጋር በመሆን ሁለተኛ የብረታ ብረት ፋብሪካ ሊከፍት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኩባንያዉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ባደገ ከበደ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ በተለይ እንደገለፁት ኩባንያዉ በአዲስ አበባ ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ ኤስ ኤች (SH Steel) የተባለ የብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ አጠናቅቆ ጨርሷል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ባደገ ገለፃ በ11 ሚሊዮን ዶላር የተገነባዉ ፋብሪካ የዉጭ ኢንቨስተሮች ድርሻ 40% አድርጎ ቀሪዉ በኩባንያዉ 60% የተያዘ ነዉ ብለዋል፡፡ፋብሪካዉም ስራ ሲጀምር ለ200 ሰራተኞች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም ደረጃ ምርትን ለማስፋፋት የሚፈልገው ኩባንያዉ ዋናዉ አላማም የስራ አድል መፍጠር እና የኢንቨስትመንት ማስፋፋት ነዉ ያሉት አቶ ባደገ ኩባንያዉም በየአመቱ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እንደሚሰራ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ አስታዉቀዋል፡፡

ኩባንያዉ የቡና ምርት ወደ ዉጪ በመላክ የዉጭ ምንዛሬ እያስገኘ እንደሆነ የገለፁት አቶ ባደገ ኩባንያቸዉ የጥረጥሬ ምርቶችን ለማምረት ዝግጅቱን ጨርሷል ብለዋል፡፡በተጨማሪም ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶች የመሬት አቅርቦት መንግስት ቢያመቻች ለኢንደስትሪ እድገት እደሚረዳም ገልፀዋል፡፡

ዋልያ ብረታ ብረት የሲሳይ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እህት ኩባንያ ሲሆን በስሩም ቤስት ቀለም ፋብሪካ፡ቤስት ፕላስቲክ ኢንደስትሪ፡ቤስት የፕላስቲክ ቱቦ ማምረቻ ኢንደስትሪ፡የሰበታ ማእድን ዉሃ፡ሆራይዘን አጠቃላይ ኮንስትራክሽን እና አጃንባ ሪል እስቴት ይገኙበታል፡፡ ዋልያ ብረታ ብረት ኢንደስትሪ ከ1000 ለሚበልጡ ስራተኞች የስራ አድል እንደፈጠረም ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ባደገ ከበደ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትጵያ ተናግረዋል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=GSlcZJfFU8o[/embedyt]

Related Post