አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ከ99 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዘ

ከ99 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዘ
ከ99 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዘ

በድሬድዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከ99.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትባንድ እቃዎች የመኪና መለዋወጫ፣ ጎማዎች፣ አዳዲስ አልባሳት ፣ ጫማዎች፣ የቤት ዕቃዎች እና ምግብ ነክ እቃዎች ናቸው፡፡
እነዚህ የኮንትሮባንድ እቃዎች ወደ ድሬድዋ ከተማ ሲጓጓዙ አዲጋላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች፣ የፌዴራል ፖሊስ ፀረ ኮንትሮባንድ አባላት እንዲሁም ከሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በጋራ በመሆን በተደረገ ቅንጅታዊ ሥራ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ ለጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች፣ ለየፌዴራል ፖሊስ ፀረ ኮንትሮባንድ አባላት፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲሁም መረጃውን በመስጠት ትብብር ላደረጉ ለአካባቢው ህብረተሰብ ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
https://youtu.be/GEPUH2Zn4Pc

Related Post