ምክር ቤቱ ባካሄደው 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ውጭ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
ይህ የተገለጸው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎችን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ በቀረበበት ወቅት ነው፡፡ ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳቡን ያቀረቡት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ እንዳሉት በቫይረሱ ምክንያት በተለይም የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተናግረዋል፡፡
ተቋማቱን ወደ መደበኛ ስራቸው ለመመለስ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተጀመሩ መሆኑን የጠቆሙት ወ/ሮ አበባ ቫይረሱ በስፖርቱ ዘርፍም እንቅስቃሴዎችን በመገደቡ ምክንያት ሃገራችን ከአለምና ከአህጉራዊ ዉድድሮች ውጭ ልትሆን እንደምትችል አብራርተዋል፡፡
ቫይረሱን እየተከላከሉ ስልጠናዎችንና ዉድድሮችን ለማስቀጠል የሚያስችሉ መመሪያዎች ተዘጋጅተው በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የቅደመ- ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ሰብሳቢዋ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡