አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

ከ23 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኮቪድ-19 መከላከያ መከተባቸው ተገለጸ

ከ23 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኮቪድ-19 መከላከያ መከተባቸው ተገለጸ

በመጀመሪያ ዙር ከተከተቡት 10 ሚሊዮን ሰዎች ጋር እስካሁን 23 ነጥብ 3 ሰዎች እስካሁን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት መከተባቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሁለተኛው ዙር የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከየካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 22 ቀን ድረስ ከ13 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በጤና ሚኒስቴር የብሔራዊ ክትባት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮሐንስ ላቀው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ሁለተኛው ዙር የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በአብዛኛዎቹ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት ከ13 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ክትባቱን ወስደዋል።



በዚህ ዘመቻ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን በክትባት ተደራሽ ለማድረግ ዕቅድ መያዙንም ጠቅሰው፤በአሁኑ ጊዜም ቀሪ ስድስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶዝ ክትባቶች ለኅብረተሰቡ እየተሰጡ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

በተባለው ቀን ዘመቻውን ያልጀመሩ ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎችም ክትባቱን በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። ክልሎች አስቻይ ሁኔታዎችን እያዩ ዘመቻውን እንዲያከናውኑ እየተደረገ እንደሚገኝም የተናገሩት አስተባባሪው፤ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል 30 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ዝግጁ በመሆኑ በዘመቻው ከተያዘው 20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሊከተቡ የሚችሉበት ዕድል እንዳለም አብራርተዋል።

Related Post