አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ከ11ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

ከ11ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ
ከ11ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግንባታ አሸዋ ውስጥ ተደብቀው በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ግምታዊ ዋጋቸው ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

የአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአዋሽ ከተማ አካባቢ እና በአልበረከቴ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ባደረገው ክትትል በግንባታ አሸዋ እና ጠጠር ተደብቀው ሊያልፉ የነበሩ ግምታዊ ዋጋቸው ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ አልባሳት ፣ መድኃኒቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
በተመሳሳይ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የቁም እንስሳቶች፣ እርጥብ ጫት፣ አልባሳት እና የትንባሆ ምርቶች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተይዘዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ አመራሮች እና ሰራተኞች ለፌደራል ፖሊስ አባላት እና ለየአካባቢዎቹ የጸጥታ አካላት ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Related Post