አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ከግብርና ምርቶች ከ600 ሚሊዮን በላይ የውጪ ምንዛሪ ተገኘ

ከግብርና ምርቶች ከ600 ሚሊዮን በላይ የውጪ ምንዛሪ ተገኘ

በ2012 በጀት ዓመት 9 ወራት ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ክትትል ከሚያደርግባቸው የግብርና ምርች ከ600 ሚሊዮን በላይ የውጪ ምንዛሪ መገኘቱን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ 9 ወራት 690,840 ቶን ምርት ለውጪ ገበያ በማቅረብ 818,611,770 ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 473,959.69 ቶን ምርት ተልኮ 658,200,550 የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷ፡፡

255,340 ቶን የቅባት እህሎች በመላክ 339,718,000 ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 162,782 ቶን ተልኮ 240,775,740 ዶላር፣ 367,189 ቶን የጥራጥሬ ሰብሎች በመላክ 231,329,070 ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 249,637.44 ቶን ተልኮ 154,663,650 ዶላር እንዲሁም 1,203 ቶን የተፈጥሮ ሙጫና እጣን በመላክ 4,164,000 ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 977.15 ቶን ተልኮ 4,204,600 ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

በተመሳሳይ 46,232 ቶን ጫት በመላክ 240,406,000 ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 44,930.26 ቶን ተልኮ 256,0373,10 ዶላር፣ 657 ቶን የብዕርና አገዳ እህሎች በመላክ 618000 የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት ታቅዶ 927.97 ቶን በመላክ 969,310 ዶላር የተገኘ ሲሆን ከባህር ዛፍ 2,376,700 የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት ታቅዶ 1,549,930 ዶላር መገኘቱንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

Related Post