አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

ከወጪ ንግድ 2.09 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

ከወጪ ንግድ 2.09 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ
ከወጪ ንግድ 2.09 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

በ2012 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት 2.68 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 2.09 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

አፈፃጸሙ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 1.9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ጋር ሲነፃጸር የ10 በመቶ ጭማሪ ያለው ሲሆን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአለም ደረጃ የንግድ ግንኙነት የተቀዛቀዘ ቢሆንም ኢትዮጵያ እያመረተች ያለችው ለምግብነት የሚውሉ ምርቶች በመሆናቸው ገቢው ሊጨምር ችሏል ያሉት በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኩሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ናቸው፡፡

አቶ ወንድሙ እንደገለጹት አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ጫት በዘጠኝ ወራት ከተያዘላቸው እቅድ በላይ አፈፃጸም ያስመዘገቡ ሲሆን የብዕርና አገዳ እህሎች፣ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን፣ ቡና፣ ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም ጨርቃጨርቅና አልባሳት የእቅዳቸውን ከ75 በመቶ በላይ፣ ታንታለም፣ የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ ስጋ፣ ቅመማ ቅመም፣ ባህር ዛፍ እና ሻይ ቅጠል የእቅዳቸውን ከ50 እስከ 74 በመቶ ገቢ አስገኝተዋል፡፡ በሌላ በአንፃሩ ወርቅ፣ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እና የቁም እንሰሳት የእቅዳቸውን ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ገቢ ያስገኙ ምርቶች ናቸው፡፡

Related Post