አርእስተ ዜና
Sun. Jan 26th, 2025

ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 ገቢዉን 164 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዷል

ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 ገቢዉን 164 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዷል
ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 ገቢዉን 164 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዷል

ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት ገቢዉን 163.7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ማቀዱን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ።

“፡ገቢን ከማሳደግ አኳያ ከመደበኛ የቴሌኮም ገቢ ምንጮች በተጨማሪ ሌሎች እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶችን በመጨመር፣ ዲጅታል፣ አዳዲስ እና የተሻሻሉ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አገልግሎቶችን ለገበያ በማቅረብ፣ የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽንስ፣ የቴሌብር ተደራሽነትና የአገልግሎት አይነቶች እንዲሁም አጋሮችን በማሳደግ፣የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል እና የደንበኛ እርካታን፣ ቆይታንና ታማኝነትን በማሳደግ በ2016 በጀት ዓመት የተገኘውን 93 ቢሊየን ብር ገቢ በ74.7% በማሳደግ 163.7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዷል፡፡”

ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የደንበኞችን ብዛት በ6% በመጨመር 83 ሚሊዮን ለማድረስ ያቀደ ሲሆን የሞባይል ደንበኞችን በ5.5% በመጨመር 79.7 ሚሊዮን ማድረስ፣ አልሟል። በተጨማሪም የሞባይል ዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በ16% በመጨመር 47.4 ሚሊዮን ማድረስ እና የፊክስድ ብሮድባንድ ደንበኞችን በ25% በመጨመር 934 ሺህ በማድረስ አጠቃላይ የቴሌኮም ስርጸት መጠንን 73% ለማድረስ ማቀድን ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ኩባንያችን ባለፈው በጀት ዓመት ላስመዘገበው የላቀ ውጤት አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ደንበኞቻችን፣ የኩባንያችን የስራ አጋሮች፤ የምርትና አገልግሎቶቻችን አከፋፋይ ወኪሎች፣ አቅራቢዎች፣ ቬንደሮች፣ የሚዲያ አጋሮቻችን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ እያልን፣ በዚህኛው በጀት አመትም የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ ከኩባንያችን ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን፡፡

Related Post