አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

ኢትዮጵያ 163 ቢሊየን ብር የቀረጥ ገቢ ሰበሰበች

ኢትዮጵያ 163 ቢሊየን ብር የቀረጥ ገቢ ሰበሰበች
ኢትዮጵያ 163 ቢሊየን ብር የቀረጥ ገቢ ሰበሰበች

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት 166.52 ቢሊየን ብር የቀረጥ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 162.99 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 97.88 በመቶ ማሳካት መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ገልፀዋል፡፡

እንደ (ገቢዎች ሚኒስቴር ዘገባ ከሆነ የሚኒስቴሩ የአራት ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የቅ/ፅ/ቤቶች ስራ አስኪያጆችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል፡፡

በግምገማው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ባለፉት አራት ወራት የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር የ31.5 በመቶ ወይም የ39.04 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ገልፀው አጠቃላይ ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 105.24 ቢሊየን ብር የሚሆነው ከሀገር ውስጥ ታክስ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን ቀሪው 57.74 ቢሊየን ብር ደግሞ ከወጪ ንግድ ቀረጥ እና ታክስ የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተቋሙን የአራት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የፕላንና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ታደሰ በበኩላቸው ባለፉት አራት ወራት በህገ-ወጦች አማካኝነት መንግስት ሊያጣው የነበረን 11.169 ቢሊየን ብር ገቢ በተሰሩ የታክስ ኦዲት ስራዎች ማዳን መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ተቋሙ ባለፉት አራት ወራት ከአዲስ እና ከቆየ የታክስ ዕዳ 11.10 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 12.72 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 114.56 በመቶ ማሳካት መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡

Related Post