አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ልትጀምር ነዉ

ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ልትጀምር ነዉ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 93ኛ መደበኛ ስብሰባ በካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ያደገና የዳበረ የካፒታል ገበያ ለሃገር ኢኮኖሚ ዕድገትና ብልፅግና እጅግ በጣም አስፈላጊ በማለት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አብራርቷል፡፡

“የካፒታል ገበያ ባደገበት ሃገር አምራች ኩባንያዎች የአክስዮንና የብድር ሠነዶችን በመሸጥ የረዥም ጊዜ እና የአደጋ ሥጋት ያለባቸውን ነገር ግን የምርታማነት ባህሪ ያላቸው ኘሮጀክቶች በቀላሉ ፋይናንስ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የካፒታል ገበያ ለህብረተሰቡ አማራጭ የቁጠባ መንገዶችን በማቅረብ የኢኮኖሚውን የፋይናንስ ቁጠባ ከፍ ያደርገዋል፡፡”

“ይህም ኢንቨስትመንትን በሃገር ውስጥ ቁጠባ ፋይናንስ እንዲሆን በማድረግ ከውጭ ፋይናንስ ያለንን ጥገኝነት ይቀንሰዋል፡፡ በዚህ ረገድ የካፒታል ገበያ የሃገሪቱን የክፍያ ሚዛን በማስተካከል ለማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ እነዚህንና ሌሎች የካፒታል ገበያ ጥቅሞችን ታሳቢ በማድረግ ረቂቅ አዋጁ በብሄራዊ ባንክ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመራ ወስኗል፡፡”

Related Post