አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ኢትዮጵያ እና ቻይና በኢንቨስትምንት አማራጮች ዙሪያ ተወያዩ

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በቻይናው የፋይናንስ ምክትል ሚኒስትር ሊያው ሚን የተመራ ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የውይይቱ ዋና ትኩረትም በሁለቱ ሀገራት መካለል ያለው የኢንቨስትመንት ትስስር ይበልጥ በማጠናከር የተሻለ ኢኮኖሚያዊ እድገት ማምጣት እንደ ሆነ ተጠቁሟል፡፡ ኢንደስትሪላይዜሽንን ለማምጣት ከፖሊሲ እና ስትራቴጂ ዝግጅት ጀምሮ ከቻይና መንግስት መልካም ተሞክሮዎችን ወስደናል ያሉት የኢንዱትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ዘላቂና ቀጣይነት ያለው እድገት ላማምጣትም የግሉን ዘርፍ በአስፈላጊ ሁኔታዎች ለመደገፍ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የግልን ዘርፉን የሚያበረታታ እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የኢንቨስትመንት ትስስር የሚያጠናክር ፖሊስ መኖሩን ጨምሮ እንደ ሀገር በርካታ የኢንቨስትመንት መደላድሎች እንዳሉ የገለጹት አቶ መላኩ አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ድጋፎች፣ አቅም ያላቸው አዳዲስ ባላሃብቶችን በመሳብ፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ምጣኔ ሃብት ሚዛናዊ በማድረገ ፣ የሁለትዮሽ ንግድ ግንኙነት ማጠናከር እና የተለያዩ የመሰረት ልማት ድጋፎችን የቻይና መንግስት ድጋፍ እንዲያደርገ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለው ሀገራዊ የምርት እድገት የሚያበረታታ ነው ያሉት የቻይናው የፋይናንስ ምክትል ሚኒስትር ሊያው ሚን ሀገራቸው የተለያዩ ኢንቨስትመንትችን በተመለከተ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት እየተንቃሳቀሰ መሆኑንና ኢትዮጵያም ዋና መዳረሻ ሀገር አድረገው እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ምክትል ሚኒስትሩ አክለውም የአገሪቱን ኢንዱስትሪያለይዜሽን ለማፋጠንም በአይስቲ ዘርፍ የቻይናውያን ባላሃብቶች ተሳትፎ ቢያደርጉ አዋጭ እንደሚያደርጋቸው ጠቁመው በሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮችም ባለሃብቶች እንዲሰማሩ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Related Post